ሳምንታዊዉ ስፖርት
ሰኞ፣ ጥር 26 2006ማስታወቂያ
ባን ኪ ሙን፤ ስፖርትና ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፤ ለኅብረተሰቡ በሚያበረክቱት ድርሻ መጠን ላይ በሚካሄደው ክርክር ተሳታፊ ይሆናሉ።
ለአካል ብሎም ለመንፈስ ጥንካሬ የሚበጀው ስፖርት ፣አንዳንድ እስፖርተኞች፤ በጥረትም ሆነ ችሎታ ሳይሆን አስነዋሪና ጎጂ በሆነ መልኩ በጉልበት ሰጪ መድኃኒት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ራስ ምታት ሆኖ መቆየቱ የሚታበል አይደለም። ምርመራውም ሆነ ክትትሉ ተጠናክሮ ቢቀጥልም፤ ሥጋቱ አልተወገደም። የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ ፣ ለጡንቻ ጥንካሬ የሚሰጥ አዲስ ሰው ሠራሽ ጉልበት ሰጪ ቅመም ስለመገኘቱ
ማብራሪያ ሰጥቷል። ይህን ለመገንዘብ የበቁት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፤ ጀርመናዊው ቶማስ ባህ፤ በፀረ ጉልበት ሰጪ ቅመማት ምርምር ላይ ያተኮረው ድርጅት ምንጊዜም ተከታትሎ እንደሚያከሽፈው ጸኑ እምነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ወደ ሳምንታዊው የእስፖርት ዝግጅታችን እናምራ
ሐና ደምሴ---
ተክሌ የኋላ