1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ቻይና ልዑካን የትግራይ ክልል መንግስት ወቀሳ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2012

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ያልታወቀ የፌደራል መንግስት አካል የቻይና ሻንዢ ግዛት ባለስልጣናትና ኢንቨስተሮች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ከለከለ ሲል ከሰሰ፡፡ የክልሉ መንግስት የጉዞ ክልከላው «ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል» ብሎታል፡፡

https://p.dw.com/p/3V9XT
Tigray regional Gouvernement Emblem
ምስል Tigray Communication affairs office

«ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል» ብሎታል

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ያልታወቀ የፌደራል መንግስት አካል የቻይና ሻንዢ ግዛት ባለስልጣናትና ኢንቨስተሮች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ከለከለ ሲል ከሰሰ፡፡ የክልሉ መንግስት የጉዞ ክልከላው «ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል» ብሎታል፡፡ የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ እንደገለፀው ቻይናውያኑ በትግራይ ልያደርጉት የነበረው ጉብኝት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቀድሞ የሚያውቀውና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ነው፡፡ በዚሁ ጉዳይ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ አለው። 

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ