1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት፦ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም.

ሰኞ፣ ግንቦት 7 2015

በዛሬው የስፖርት ዝግጅታችን አትሌቲክስ፣የሳምንቱ መጨረሻ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ክለቦች እና የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ውጤቶች እና ሌሎችም ስፖርታዊ መረጃዎች ተካተዋል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ አጠናቅራዋለች።

https://p.dw.com/p/4RMfN
Manchester City - FC Arsenal
ምስል Martin Rickett/PA Wire/dpa/picture alliance

ስፖርት፦ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም.

የአርሰናል የፕሪምየም ሊግ ዋንጫውን ዘንድሮ የማንሳት የረዥም ጉዞ እቅዱ በገዛ ሜዳው በብራይተን በደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት ተጨናግፏል። በአንጻሩ የፔፕጋርድዮላው ማንቸስተር ሲቲ ኤቬርተንን ካሸነፈ በኋላ የሻምፕዮንነት እድሉን አስፍቷል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ደግሞ አሁንም በሊጉ መሪዎች በባየርን ሙኒክና በቦሪስያ ዶርትሙንድ መካከል ለሻምፕዮንነት የሚደረገው ትግል ቀጥሏል። ባርሴሎና ከልዮኔል ሜሲ ስንብት በኋላ የመጀመሪያውን የላሊጋ ውን ዋንጫ አሸናፊነቱን አረጋግጧል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ኂሩት መለሰ