ስፖርት፣ መስከረም 28፣ 2011 ዓም
ሰኞ፣ መስከረም 28 2011የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ
የአዲስ አበባ እግር ካስ ፌዴሬሽን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በየአመቱ የሚያደርገው ውድድር ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጀምራል። ለ13ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይሄው ውድድር ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዲስ አበባ ሲሳተፉ፤ ከክልል ወላይታ ዲቻ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ አዳማ ከተማና ፋሲል ከነማ እንዲሁም ከምእራብ አፍሪካዊታ የናይጀሪያው ካራ ዩናይትድ ክለብ በተጋባዝነት ይሳተፋል። ክለቡ ግብዣውን ሲቀበል ሙሉ ወጭውን ራሱ ሸፍኖ መሆኑ ተነግራል።
አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ለብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ስላስመረጠ እንደማይሳተፍ አሳውቃል።
በመክፈቻው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 3 ለ 2 ፤ መከላከያና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የነበሩ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፋል። ትናንት በተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ዲቻን ፤ ፋሲል ከነማ ጅማ አባ ጅፋርን አሸንፈዋል። በመጀመሪያ የተገናኙት ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ዲቻ 2 ለ 0 ሲለያዩi ፋሲል ከነማ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተለያይታል። ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜና እሁድም ይቀጥላል።
አትሌቲክስ
ትናንት በዩኤስ አሜሪካ፣ በቺጋጎ ከተማ በተደረገው የማራቶን አትሌቲክስ ሩጫ ብሪታንያዊው ሞ ፋራህ አሸንፋል። በሁለት ሰከንድ ኢትዮጵያውን ሙስነት ገረመውን ቀድሞ በመግባት አሸናፊ ሆናል።
ሞ ፋራህ የመጀመሪያ የሆነነውን የማራቶን ድሉን በ 2 ሰዓት : 5: 11 ጨርሶ ሲያጠናቅቅ ፤ ኢትዮጵያዊው ሞሲነት ገረመው 2: 5: 13 እጅግ አንዱ አንዱን ለማስቀረት ፍክክሩ ያየለበት ነበት። ጃፓናዊው ሱጉሩ ኦሳኮ 2: 5: 50 ተከትሎ በ3ኛነት አጠናቋል። ይህ የሞፋራህ ድል የአውሮጳ አዲስ ሬከርድ ሆኗል። ፋራህ ቀዝቃዛና ዝናብ የነበረውን የቀኑ የአየር ሁኔታ ተቃቁሞ 3ኛውን የማራቶን ድሉን አስመስዝባል።
ጨርሼ ስገባ ተደንቂያለሁ ብላል የ35 አመቱ ሞ ፋራህ። በ2012 እና 2016 እንደጎረጎረያን አቆጣጠር የ5,000 እና 10,000 ሜትር አሸናፊው ሞ ፋራህ ከ1996 ወዲህ በችጋጎ የአትሌቲክስ ምድር ያሸነፈ የመጀመሪያው ብሪታንያዊ እንደሆነ ተጠቅሳል።
በሴቶቹ ኬንያዊታ ብሪጊድ ኮስጄይ 2 18 35 በቀዳሚነት ስታሸንፍ ኢትዮጵያውያኑ ሮዛ ደረጀ 2 :21: 18 እንዲሁም ሹሬ ደምሴ 2: 22: 15 በሆነ ፍጥነት በመጨረስ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ተከታትለው ገብተዋል።
ከዚህ ቀደም ቺጋጎ እና ለንደን ላይ አሸናፊ የሆነችው የ24 አመታ ኮስጄይ ሰባት የአህጉር አጋሮቻን በማስቀረት ከ5 ኪ,ሜ ጀምሮ ከፊት በመምራት ርቀቷን በማስፋት በ1ኝነት አጠናቃለች።
ነጃት ኢብራሂም / ሃይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ