1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት

ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2009

ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ትናንት የአምስተርዳም እና የቶሮንቶ የማራቶን ውድድሮችን በአንደኝነት ጨርሰዋል ።

https://p.dw.com/p/2RLht
Fußball Bundesliga Borussia Dortmund - Hertha BSC
ምስል picture-alliance/City-Press GbR

Sport 171016 - MP3-Stereo

ትላንት በሆላንድ አምስተርዳም  አና በ ካናዳ ቶሮንቶ በተካሄዱት ሁለት የማራቶን ውድድሮች በሴቶች ኢትዮጵያውያን  አትሎቶች በወንዶች ኪንያውያን  አትሌቶች አሸንፈዋል ።በአምስተር ዳም መሰለች መልካሙ እና አብብች ፈለቀ አንደኛና ሁለተኣን ሲሆኑ በወንዶች ማራቶን   የ 24 አመቱ ኪንያዊ አትሊት ዳንየል ዋንጁሩ  የከተማውን አዲስ ሪከርድ አስመዝግቦዋል ። ኬንያውያን  ከ1 እስከ 8ኛደረጃ በመውጣት ያለ  አንዳች ጭንቀት በሮጡበት በአምስተርዳም ማራቶን  ኢትዮጵያዊያኖቹ ሙሉ ዋስ ይሁን እና አበራ ኩማ 1፡30 ስከንድ በማይሞላ ልዮነት  9ኛ እና 10ኟ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል።ዝናባማ በነበረው በቶሮንቶ  የክረምት ማራቶን ደግሞ በሲቶች ሱሪ ደምሲ እና ታደለች በቀለ ተከታትለው ገብተዋል ።በወንዶች ኪንያዊ  አትሌት ፊሊሞን ሮኖ አሸንፏል ። የጀርመን ቡንደስሊጋ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሜዳ ቴኒስ እና የብስኪሌት ውድድሮች እና ውጤቶቻቸው በስፖርት ዝግጅታችን ተካተዋል ።

ሃና ደምሴ

ኂሩት መለሰ