ስፖርት
ሰኞ፣ ነሐሴ 2 2008ሐምሌ 29 በተጀመረው የኦሎምፒክ ጨዋታ ከ207 ሀገራት የመጡ 11 493 አትሌቶች እስከ ነሀሴ 15 ፣ በ28 የስፖርት አይነቶች ሲወዳደሩ ይቆዩበታል ።ለሜዳልያ የሚደረግው ትግል በ 32 የተለያዩ የመወዳደሪያ ስፍራዎች ይካሂዳሉ፥ ተጨማሪ 5 የብራዚል ከተሞች ደግሞ የእግር ኳስ ውድድሮችን ያስተናግዳሉ ። 2 102 የወርቅ የብር እነ የነሐስ ሜዳልያዎች ባለድሎችን ይጠብቃሉ። በተለያዮ ሀገራት በተፈጠሩ ጦርነቶችሳቦያ በአሳዛኝ ሁኒታ ሀገር አልባ የሆነ ቡድን ለመጀመሪያ ግዚ የኦሎምፒክን አርማ በመያዝ ተሳታፊ ሆነዋል ። በወንዶች 400 ሜትር የነጠላ ውሐዋና ውድድር ጃፓን የወርቅ እና የንሀስ ሚዳልያ ስታገኝ አሚሪካ የብር ሚዳልያ ወስዳለች ። በሴቶች ተመሳሳይ ውድድር ሀንጋሪ የወርቅ አሚሪካ የብር ስፒን የንሀስ ሚዳልያ አግኝተዋል ። በወንዶች 400ሚትር የነጻ ውሀ ዋና ውድድር አውስትራልያ የወርቅ ሚዳልያ አግኝታልች። በሴቶች የ4 በ 100 ሚትር ውሀ ዋና ውድድር አውስትራልያ አሜሪካ እና ካናዳ አሻንፈዋል።በወንዶች የጎዳና ብስክሌት ውድድር በቤልጅየም ቢስክሌተኛ አሸናፊነት ተጠናቅዋል በጁዶ ውድድር ሩሲያ የወርቅ ሚዳልያ ኣጥልቃች።ከ ኦሎምፒክ መ ድረክ ሙሉ በሙሉ ትታገድ አትታግድ ስትባል የክረምችው የራሺያም ህዝብ መዝሙር ትላንት በተገኘ ድል በኦሎምፒክ መንድር መደመጥ ጀምሯል ።የጀርመን ቡድን ትላንትም ከደቡብ ኮርያ 3ለ 3 በሆነ ውጤት አቻ ወጥቶዋል።
በ ምድብ ዲ አርጀንቲናን 2 ለ 0 የረታው ያአውሮፓ ሻንፒዮን ፖርቹጋል ትላንትም ሆንዱራስን 2 ለ1 ረትዋል ።ሆንዱራስ 3 ለ2 የተረቱት የሰሚን አፍሪካዎቹ አልጀሪያዎች በአርጀንቲና 2ለ1 ተሸንፈው ከውድድር ውጭ ሆነዋል ።ኣልጅሪያ ፉጂ ሲውድን እና ደቡብ አፍሪካ አስቀድመው ከአኦሎምፒክ እግርኩዋስ ጨዋታ ውድድር ውጭ የሆኑ ሀገሮች ሆነዋል ።በሴቶች ያእግር ኩዋስ ጨዋታ ብራዚል ሲውድንን 5 ለ 1 ኒውዝላንድ ኮሎንቢያን 1 ለ0 ሲያሸንፉ ቅዳሜ እለት ደቡብ አፍሪካ በቻይና የሴቶች ብድን 2ለ0 ካናዳ ዝምባቢየን 3ለ1ረተዋል። ጀርመን ከአውስትራልያ 2ለ2 ሲለያዩ አሚሪካ ፈረንሳይን 1ለ 0 አሸንፎዋል ። በሪዮ ኦሎምፒክ የሚዳቲንስ ጨዋታ ኖቫክ ጃኮቪች በመጀመሪያው ዙር በ ጁዋን ማርቲን ዲል ፖትሮ ተረቶ ከውድድር ውጭ ሆንዋል ስርቢያዊው ጃኮቪች ለአርጀንቲው ዲል ፖትሮ እጅ የሰጠው ሁለት ግዜ 7 ለ6 በሆነ ውጤት ተረቶ ነው።ሁለቱ የዊልያምስ ልጆች ቪንስ እና ሰሪና ዊልያምስ እንደዚሁ በአስደንጋጭ ሁኒታ ከጥንድ የሚዳቲንስ ውድድር ውጭ ሆነዋልየኦሎምፒክ የጥንድ ውድድር አሸናፊነት ለመጅመሪያ ጊዜ ከውድድር ውጭ የሆኑት ቪንስ እና ሰሪና ዊልያምስ በቺክ ሪፖብሊክ ተወዳዳሪዎች ሉዊስ ሳፋሮቫ እና ባራቦራ 6ለ3 እና 6 ለ 4 ተረተው ነው ።ዛሪ አራተኛ ቀኑን በ ያዘው ውድድር 562 አትሊቶችን ያቀፈውብራዚል የሚገኛው የ አሚሪካ ኦሎምፒክ ቡድን በ 3 የወርቅ 5 የብር በ 4 የነሀስ ሚዳልያ በአጠቃላይ 12 ሚዳልያ መሪነቱን ሲይዙ ቻይና በ 3 የ ወርቅ በሁለት የብር በ3 የነሀስ በድምሩ በ7 ሚዳልያ ሁለተኛ429 አትሌቶችን ይዛ የትጉዋዘችው አውስትራልያ ትላንት በኢላማ ተኩስ ካትሪን ስኪነር ያገኝችውን ወርቅ ጨምሮ ባ3 ያወርቅ እና በ3 ያነሀስ ሜዳልያ ባድምሩ በ 6 ሚዳልያ ለግዚው ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ሀንጋሪ በ2 የወርቅ ሜዳልያ ደቡብ ኮርያ በ 1 የወርቅ ።435 አ ትሌቶችን የያዘው የጀርመን ኦሎልፒክ ቡድን ከዛሪ ጀምሮ በሚደረጉ ውድድሮች የሚዳልያ ሰንጠረዠ ውስጥ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
የሩስያየአካል ጉዳተኞች አትሌቲክስ ቡድን ከሪዮ ያፓራ ኦሎምፒክ ውድድር ውጭ እንዲሆን ተወስነ ።
የራሺያ የአካል ጉዳተኞች አትሌቲክስ ቡድን ከውድድሩ ውጭ አንዲሆን የወሰነው የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች አትሊቲክስ ኮሚቴነው። የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ኮሚቴ በከፍተኛ ሁኒታ ሲያነጋግር የሰነበተውን የሩስያ መንግሥት አትሌቶቹ አበረታች ንጥረ ነገሮችን እንዲጠቀሙ ሁኔታዎችን ሲያመቻች መክረሙ ከተደረሰብት በኋላ ቡድኑ ሙሉ ለሙሉ ከሪዮ ኦሎምፒክ ሊታገድ ይችላል የሚለውን ሐሳብ ውድቅ አድርጎ እያንዳንዱ አትሌት በተናጠል መቅጣቱ ይታወሳል ። ነገር ግን ዓለም አቀፉ የፓራ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የራሽያን የአካል ጉዳተኛ ቡድን ሙሉ በሙሉ ከሪዮ ኦሎምፒክ ማገዱን ትላንት አስታውቆዋል። በመጭው ወር ሪዮ ከሚካሂደው የፓራ አኦሎምፒክ ውጭ የሆነው ራሺያ የአካል ጉዳተኞች ቡድን ውሳኒውን ይግባኝ ለማልት 31 ቀናቶች ይቃሩታል። እስክዛው ግን በ18 የስፖርት አይቶች ይካፈሉ የነብሩ 267 የ ራሺያ የአካል ጉዳተኛ ቡድን ከሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ውጭ ሆነዋል ።እንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ቡድኖች አዲሱ የውድድር ዘመን የፊታችን ቅዳሜ ከመጀመሩ በፊት የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታቸውን አካሂደዋል ።
ፓውሎ ፓጎባ ወደ ቀድሞ ቤቱ ወደ ኦልትራ ፎርድ እንደሚመለስ ተነግረ ዛሪ ማልዳ ክሚያድርግው የህክምና ውጢት በሁዋለ በድጋሚ የቀድሞ ቡድኑን ይቀላቀላል፥ በ105 ሚልየን ኤሮ ወይም በ89 ሚልየን የእንግሊዝ ፓውንድ ይህ የአለም ተጫዋቾችን የዝውውር ክብረወሰን የስብረው የገንዘብ መጠን የብዙሀኑን ቅንድብ ሽቅብ ስብስቧል።
ሃና ደምሴ
ኂሩት መለሰ