1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳምንቱ ስፖርት ጥንቅር

ሰኞ፣ ግንቦት 28 2009

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ10 ሳምንት በኋላ በለንደን በሚደረገው የዓለም ሻንፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ተካፋይ የሚሆኑትን አትሌቶች በሁለቱም ፃታ ከነተመረጡበት መስፈርት ዝርዝር  ይፋ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/2e9Sz
Äthiopisches Sport Festival in Berlin
ምስል DW/Y.MH

ስፖርት 050617

ቀነኒሳ በቀለ ፥ ታምራት ቶላ ፥ ፀጋዪ መኮንን የማነ ፀጋዪ እና ሙሲ ዋስ ይሁን በወንዶች፤ በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ ፣ ብርሃኔ ዲባባ፥ ሹሬ ደምሴ፥ አሰለፈች መርጊያ  እና አማኒ ጎበና ተመርጠዋል።  የዓለም አትሌቲክስ  ማኅበር  ከራሺያ አትሌቶች ከቀረበለት የ ውድድር እንሳተፍ ጥያቂ የ28ቱን ውድቅ ማድረጉን እና የሦስቱን ብቻ መቀበሉን አስታውቋል። ተጨማሪ የ 27 አትሌቶች ጉዳይም  በምርመራ ላይ አንደሆነ ተገልጿል ። ራሺያ አትሌቲክስ ማኅበር በዓለም አቀፍ የፀረ ጉልበት ሰጭ በመታገዱ ከ ሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ውጭ አንደነበር  ይታወሳል አገዳው ከ10 ሳምንት በኋላ በለንደን የሚደረገውን የዓለም አትሌቲክስ ሻንፒዮናን ይጨምራል ።

 በአውሮጳ እግር ኳስ ፊዴሬሽን ማኅበር በየአመቱ የሚዘጋጀው የአውሮጳ ክለቦች ሻንፒየ ጨዋታ በማድሪድ አሽናፊነት ተጠናቋል። ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚውን  ጁቬንቱስን 4 ለ 1 በመርታት የአውሮጳ የእግር ኳስ ማኅበርን ታላቅ ዋንጫ በተካታታይ ለ3 ኛ ግዜ ወስዷል።

 የኢትዮ-ጀርመን የባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን  ባሳለፍነዉ የሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ እሁድን በዋና ከተማዋ በርሊን ላይ የስፖርት ፌስቲቫል አካሂዷል። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በቡድንና በየግልም የበዓሉ ተሳታፊዎች ነበሩ።

ሃና ደምሴ/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ