1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በህዝበ ውሳኔው ዙሪያ የዎላይታ እና የጋሞ ዞን ነዋሪዎች አስተያየት

እሑድ፣ ጥር 28 2015

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ነገ በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከ3 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ድምፅ የሚሰጥባቸው ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ ፣ደቡብ ኦሞ ፣ጌዴኦ ዞኖችና አማሮ ፣ቡርጂ ፣ደራሼ፣አሌና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡ የዶቼ ቬለ ዘጋቢ የዎላይታና የጋሞ ዞን ነዋሪዎችን አስተያየት አሰባስቧል

https://p.dw.com/p/4N7fH
Äthiopien - Arba Minch
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በህዝበ ውሳኔው ዙሪያ የዎላይታ እና የጋሞ ዞን ነዋሪዎች አስተያየት

በደቡብ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ነገ ጥር 29 2015 ዓም በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከ3ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የህዝበ ውሳኔ ድምፅ የሚሰጥባቸው የዎላይታ ፣ ጋሞ ፣ ጎፋ ፣ ኮንሶ ፣ ደቡብ ኦሞ ፣ ጌዴኦ ዞኖችና እንዲሁም አማሮ ፣ ቡርጂ ፣ ደራሼ ፣ አሌ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ናቸው ፡፡
በህዝበ ውሳኔው ዞኖቹና ልዩ ወረዳዎቹ በአንድ የጋራ ክልል ሥር እንዲዋቀሩ  “ እደግፋለው“ ወይም “ አልደግፍም “ በሚሉ አማራጮች  ላይ ድምፅ ይሰጥባቸዋል፡፡
የዶቼ ቬለ DW ዘጋቢ ሸዋንግዛው ወጋየሁ  ህዝበ ውሳኔው ከሚካሄድባቸው ዞኖች መካከል የዎላይታ እና የጋሞ ዞን ነዋሪዎችን አስተያየት እንደሚከተለው አሰባስቧል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

እሸቴ በቀለ