1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የጅምላ እስር አቤቱታ

ሰኞ፣ ግንቦት 22 2014

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ የጅምላ እሥር እየተፈጸመብን ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በአካባቢው እስከአሁን ከ 1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን ያረጋገጡት ባለሥልጣናቱ በክልሉ ህዝብ እንወክላለን በሚል ሁከት እየቀሰቀሱ ይገኛሉ ያሏቸውን ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን መንግሥታቸው ከእንግዲህ አይታገስም ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4C3YH
Äthiopien | Hawassa City
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በደቡብ ክልል የጅምላ እስር አቤቱታ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ የጅምላ እሥር እየተፈጸመብን ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት በበኩላቸው በልዩ ወረዳው እየታሠሩ የሚገኙት በአስተዳደራዊ መዋቅር ጥያቄ ሰበብ  የክልሉን ሰላም በማወክና በፀጥታ አባላት ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ ናቸው ይላሉ፡፡ በአካባቢው እስከአሁን ከ 1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች መታሰራቸውን ያረጋገጡት ባለሥልጣናቱ በክልሉ ህዝብ እንወክላለን በሚል ሁከት እየቀሰቀሱ ይገኛሉ ያሏቸውን ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን መንግሥታቸው ከእንግዲህ  አይታገስም ብለዋል፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ