1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈገግታ የታጀበው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች ግንኙነት

እሑድ፣ ሐምሌ 1 2010

ለሁለት አስርት አመታት ገደማ በባላንጣነት ይተያዩ የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ሲተቃቀፉ ታዩ። በእርግጥ በድንበር ይገባኛል ውዝግብ ለረዥም አመታት በአይነ ቁራኛ ሲተያዩ ለቆዩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ታሪካዊ ቀን ሆኗል።

https://p.dw.com/p/311yW
Äthiopischer Ministerpräsident Abiy Ahmed beim Staatsbesuch in Eritrea
ምስል Twitter/@fitsumaregaa

ለሁለት አስርት አመታት ገደማ በባላንጣነት ይተያዩ የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ሲተቃቀፉ ታዩ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድን ሲቀበሉ ፈገግታ እና ሳቅ ጭፈራም ይታይ ነበር። በእርግጥ በድንበር ይገባኛል ውዝግብ ከቀሰቀሰው ጦርነት በኋላ ለረዥም አመታት በአይነ ቁራኛ ሲተያዩ ለቆዩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ታሪካዊ ቀን ሆኗል።

የኤርትራው ማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በግል የትዊተር ገፃቸው "እውነተኛ ታሪካዊ ጊዜ"ብለውታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስመራ ሲደርስ ከ20 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የማስታወቂያ ምኒስትሩ ገልጸዋል።

Äthiopischer Ministerpräsident Abiy Ahmed beim Staatsbesuch in Eritrea
ምስል Twitter/@fitsumaregaa

ሁለቱ መሪዎች በአስመራ ጎዳናዎች በአጀብ ሲጓዙ ታይተዋል። ግራና ቀኝ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ምስሎች የታተሙባቸው ቲ ሸርቶች የለበሱ ኤርትራውያን ነበሩ።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንን ለመቀበል በርካታ ኤርትራውያን አደባባይ ወጥተዋል። በአስመራ ጎዳናዎች የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማዎች ጎን ለጎን ተውለብልበዋል።