ተጠርጣሪዉ ሰዉ አሸጋጋሪ ፍርድ ቤት ቀረበ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 20 2009ማስታወቂያ
የኢጣሊያ ሕግ አስከባሪዎች አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ ያሸጋግራል በማለት ያሰሩት ኤርትራዊ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ።ታሰሪዉ እና ቤተሰቦቹ፤ ግለሰቡ የታሰረዉ በስሕተት ነዉ ባዮች ናቸዉ።ኢጣሊያን ጨምሮ የአዉሮጳ መንግስታት በሰዉ አሸጋጋሪዎች ላይ ጠንከራ ርምጃ እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ ቢዝቱም ኢጣሊያ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር እያሻቀበ ነዉ።የሜድትራኒያንን ባሕር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሰጥመዉ የሚሞቱት ሰደተኞች ቁጥርም መጨመሩንም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስታዉቀዋል።
ተኽለ እግዚ ገብረየሱስ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ