1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስለኤርትራ

ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2011

በተለያዩ የውጭ ሃገራት በስደት የሚገኙ ኤርትራውያን መንግሥታቸውን በመተቸታቸው የተለያዩ ማስፈራሪያ እና ጫናዎች እንደሚደርሱባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አመለከተ።

https://p.dw.com/p/3LCY8
Logo von Amnesty International

የመንግሥት ተቺዎች ጫና ይደርስባቸዋል

ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ኤርትራን የተመለከተ ዘገባው ድርጊቱ በኤርትራ መብት ተቆርቋሪዎች ላይ የሚፈጸመው በውጭ በስደት በሚገኙ መሰል ኤርትራውያን እና በኤምባሲዎችም አማካኝነት ነው። በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አባል  የሆነችው ኤርትራ መንግሥት ይህን ድርጊት እንዲያስቆም አምነስቲ ዘይቋል። በድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ የሰብኦዊ መብት ተመራማሪ የሆኑትን አቶ ፍስሃ ተክሌን በጉዳዩ ላይ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ