አዲሱ የጀርመን መንግሥት መርኃ ግብር
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2014ማስታወቂያ
የጀርመን አዲሱ መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልትስ በፌዴራል ጀርመን ምክር ቤት (Bundestag)ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የሦስትዮች አዲስ መንግሥታቸው መርኃግብር ኮሮና፤ የፈላሲያን ጉዳይ፤ የክፍያ ዝቅተኛ ገደብ፤ የከባቢ አየርን የመሳሰሉ ጉዳዮችን አንስተዋል። የውጭ ጉዳያቸውን በተመለከተም ከሩስያ እና ቻይና ጋር ስላላቸው ግንኙነትም ንግግር አሰምተዋል።እፍኝ የማይሞሉ ያሏቸውን ቀኝ አክራሪዎችን እንደሚታገሉ ለአውሮጳ አንድነት እንደሚተጉም ገልጠዋል። ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በዚሁ ጉዳይ ላይ የቤርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጋር በስልክ ደውዬ አነጋግሬዋለሁ። መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልትስ ከቀድሞዋ መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጥምር መንግሥት አንጻር በተጠቀሱት የውጭ ፖሊሲያቸው ምን ይመስላል? ለይልማ በመጀመሪያ ያቀረብኩለት ጥያቄ ነው፤ እንዲህ በማብራራት ይጀምራል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ/ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ