ኤርትራ አሜሪካና የካርሰን ቪዛ ጉዳይ
ዓርብ፣ ሰኔ 12 2001ማስታወቂያ
በአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ኤርትራ ቪዛ እንደከለከለቻቸው ሰሞኑን የተናገሩትን የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስተባበለ ። የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑ ሁለት ወር የሆናቸው ካርሰን እንዳስታወቁት ወደ ኤርትራ ለመጓዝ ዋሽንግተን ለሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ፅህፈት ቤት ፓስፖርታቸውን ቢተዉም ፥ ፓስፖርታቸው ያለቪዛ ባዶውን ተመልሶላቸዋል ። ስለ ጉዳዩ ዶይቼቬለ የጠየቃቸው የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ፍስስ ፅዮን ጴጥሮስ ይህ ከዕውነት የራቀ ነው ብለዋል ። ፣ ካርሰን ከዚህ ቀደም ኤርትራ የሶማሊያውን አልሸባብ ትረዳለች ሲሉ የከሰሱትንም ቃል አቀባይ አቶ ፍስሀ ፅዮን እንዲሁ ሀሰት ብለዋል ። ጎይቶም ቢሆን ከአስመራ
ጎይቶም ቢሆን/ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ