1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ የኢንተርኔት ገደብና የ RSF ወቀሳ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2003

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ኤርትራን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችንና አገልግሎት ሰጭዎችን በማሰርና እና በማሸማቀቅ ከሰሰ ።

https://p.dw.com/p/R9Tn

በፈረንሳይኛው ምህፃር RSF በመባል የሚጠራው ይኽው ድርጅት እንዳስታወቀው የኤርትራ መንግስት የተቃዋሚዎችንና አገዛዙን የሚተቹ በውጭ የሚኖሩ ኤርትራውያንን ድረ ገፆችን ያገደ ሲሆን በኢንተርኔት ተጠቃሚዎችም ላይ ስለላ እና ክትትል ያደርጋል ። ይህም ተጠቃሚዎችንና አገልግሎት ሰጭዎችን ፍርሃት ውስጥ በመጣሉ ምክንያት አስቀድመው በራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ እስከማድረግ እንዲደርሱ ማስገደዱ አሳሳቢ መሆኑን በድርጅቱ የአዳዲሶቹ የመገናኛ ብዙሀን ዘዴዎች ክፍል ሃላፊ ሉሲ ማሪያን ለዶቼ ቬለ አስታውቀዋል ። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዱ ወቀሳውን ፍሬ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ