1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ፦ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የታሰሩበት ዓስረኛ አመት

ዓርብ፣ መስከረም 5 2004

የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ባለመጠበቅ REPORTERS WITHOUT BORDERS የተባለው የሰብዓዊ መት ተሟጋች ድርጅት ባወጣው ዝርዝር መሰረት ኤርትራ ከ 175 አገሮች 175ተኛ ቦታን ይዛ ትገኛለች።

https://p.dw.com/p/Rm65
ምስል AP Graphics

ይህም ያለምክንያት አይደለም። ከ10 ዓመት በፊት የታሰሩ፤ ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞችና ግለሰቦች ዛሬም በስር ላይ ይገኛሉ። ይህንንም አስመልክቶ በየአገሩ ለዚህ ቀን መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ነው። አንድ ወንድማቸው የታሰሩባቸው ኤርትራዊ ከለንደን እና በጀርመን ስላለው እንቅስቃሴ ደግሞ ፤ በጀርመን የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች አስተባባሪ እና UNITED FOR ERITREA የተባለ መሐበር ሊቀመንበር የሆኑትን - አቶ ዬናስ በርሄን ልደት አበበ ይህንን መታሰቢያ ቀን ለማስታወስ ስለታቀዱ እንቅስቃሴዎች አነጋግራቸዋለች።

ልደት አበበ

ሒሩት መለሠ