800 ገደማ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሮም ከመኖሪያቸው ተባረዋል
ሰኞ፣ ነሐሴ 15 2009ማስታወቂያ
ከስደተኞቹ መካከል አንዷ የሆኑ እንስት "ቅያሬ የለንም። ልብስ አላወጣንም። ሶስት ቀን ውጭ ነው የምናድረው" ሲሉ ይናገራሉ። በድንገት ከሕንጻው እንዲወጡ መገደዳቸውንም አክለዋል። "ተጥለናል በቃ። አሁንማ ቆሻሻ ላይ ነው ያለንው" የሚሉት እኚሁ እንስት ቀጣይ እጣ ፈንታቸው ምን እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል። በሮም ከተማ ከቴርሚኒ ማዕከላዊ ባቡር ጣቢያ አጠገብ ከሚገኘው የመኖሪያ ሕንፃ ከተባሉት መካከል የሆኑ ሌላ ስደተኛ ደግሞ "ወደ አገራችን መግባት የማንችል ስደተኞች ነን። በጣም ችግረኞች ነን። አሁን ሜዳ ላይ ተጥለናል።" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
ከስደተኞቹ መካከል ከ200 በላይ የሚሆኑት በጎዳና እና አደባባይ ለመተኛት ተገደዋል። ሮም ስደተኞቹን ከሚኖሩበት ሕንፃ ለማስለቀቅ ወደ 500 ገደማ ፖሊሶች ማሰማራት አስፈልጓት ነበር። ዛሬ ወደ ቦታው ጎራ ብሎ የስደተኞቹን ሁኔታ የቃኘው የሮሙ ወኪላችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ታዝቧል።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ