1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኮሮና ወረርሽኝ ያገገመችዉ ቻይና

ማክሰኞ፣ መጋቢት 15 2012

በጎርጎረሳዉያኑ 2019 መጠናቀቅያ ቻይና ዉስጥ የተቀሰቀሰዉ የኮሮና ወረርሽ በአሁኑ ወቅት ዓለምን አዳርሶአል። በቻይና የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ጠንካራ የዝዉዉር እገዳ  ከተጣለ እና ኤኮኖሚያዊ ገቢን የሚያስገኙ ማኅበራዊ መስተጋብሮች ሁሉ ሙሉ ከተዘጉ በኋላ ዛሬ ኮሮና በሚያስከትለዉ በሽታ የሚሞተዉም ሆነ የሚለከፈዉ ሰዉ ቁጥር በመቀነሱ ተነግሮአል።

https://p.dw.com/p/3Zyfx
Coronavirus | China wird die Sperrung von Wuhan Coronavirus beenden
ምስል Getty Images/AFP/STR

ከኮሮና ወረርሽኝ ያገገመችዉ ቻይና

 

በቻይና የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት የተቀሰቀሰዉ በጎርጎረሳዉያኑ 2019 መጠናቀቅያ ላይ ነበር። የተኅዋሲዉን መዛመት ለመግታት ቻይና በሃገሪቱን ኤኮኖሚ እንቅስቃሴ እና በሰዎች ዝዉዉር ላይ ጠንካራ እገዳን ካሳረፈች  በኃላ አሁን አሁን አንዳንድ የቻይና ግዛቶች ወደ የእለት ኖሮአቸዉ እየተመለሰ ነዉ። እንድያም ሆኖ የማኅበረሰቡ ሕይወት እንደቀድሞዉ ሁሉ ተስተካክሎ ይቀጥላል የሚለዉ ተስፋ ገና ለጥያቄ የሚቀርብ  አይደለም። 

የኮሮና ቫይረስ በተቀሰቀሰበት በሁቤይ ግዛት የዝዉዉር እገዳዉ በከፊል ተነስቶ ሰዎች ቀስ በቀስ ከቤታቸዉ መዉጣት ጀምረዋል።  በዉሃን ከተማ እና በሌሎች የቻይና  ግዛቶችም እንዲሁ  የዝዉዉር እገዳዉ ላላ ብሎአል። የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቡሶች ፤ ባቡሮች እና የከርሰ ምድር ባቡሮች ሁሉ በከፊል ስራ ጀምረዋል። እንደባለሥልጣናት ገለፃ ሰዎች በተኅዋሲዉ መያዝ አለመያዛቸዉ መመርመርያ የነበሩ ኬላዎች እንኳ እየተነሱ ነዉ። እንድያም ሆኖ የሁቤይ ግዛት ነዋሪዎች አሁንም በነፃ አይንቀሳቀሱም ። የሕዝባዊትዋ ቻይና መንግሥት እና የፓርቲ አመራሮችም ይህ ብሩህ ተስፋ የሚታይበት ዉጤትን በጥንቃቄ እንደሚያዩት ይገልፃሉ።

«የመንግሥት የሆነዉ ማዕከላዊ ባንክ ምክትል ኃላፊ ቼን ዩሉ እንደተናገሩት ወረርሽኙ ያሳረፈዉ አሉታዊ ተፅኖ  ለጥቂት ግዜም ቢሆን መቀጠሉ አይቀሬ ነዉ። ለምሳሌ የመገልገያ ቁሳቁሶች ፍላጎት ጨምሮአል።  የተኅዋሲዉ ስርጭት እስከቀነሰ ድረስ የቻይና ኢኮኖሚም ያንሰራራል።»

Coronavirus | China wird die Sperrung von Wuhan Coronavirus beenden
ምስል Getty Images/AFP/STR

በቻይና ኮሮና ስርጭትን በተመለከተ ብዙ ታዛቢዎች ጥርጣሬ አላቸው ፡፡ በቤጂንግ የኢኮኖሚ  ጉዳይ ተንታኝ  ዳን ዋንግ  እንደሚሉት ማዕከላዊው መንግስት በሚፈልገዉና በክልል ግዛቶች ዉስጥ ተግባራዊ በሚሆነዉ ነገር መካከል ልዩነቶች አሉ። 

«ማዕከላዊው መንግሥት ሰዎች ወደ ሥራቸዉ እንዲመለሱ ሁሉንም ነገር ያደርጋል።  በቦታው ላይ ግን ሆነን ስናይ ግን ሥራቸዉን መቀጠል የሚፈልጉ ሰዎች እንዲሁም በከፊል ኩባንያዎች ወደየእለት ተዕለት ኑሯቸው እንዳይመለሱ ይከለከላሉ ፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የተኅዋሲዉ  መጠን እንደገና በሚያንሰራራበት ቦታ ሁሉ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጭዎች ዉሳኔ ተፈጻሚነት ስለሚያበቃ ነዉ። »

በቻይና ይፋ መረጃ መሰረት ሃገሪቱ  ውስጥ የሳንባ በሽታን በሚያሲከትለዉ  ተኅዋሲ  የተያዘ አዲስ ታማሚ የለም። ባለፈዉ እሁድ ከዉጭ ሃገራት ወደ 40 የሚሆኑ በኮሮና የተለከፉ ሰዎች ተኅዋሲዉን ወደ ሃገር ይዘዉ መግባታቸዉ ተዘግቦአል።  

ሆኖም የቻይና  ባለ ሥልጣናት ላለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ይፋዊ መረጃዎችን  ደጋግመው ይደብቁ ስለነበር ፤ መንግሥት አሁን ይፋ በሚያደርዉ መረጃና ቁጥር ላይ አብዛኞች ጥርጣሪ አላቸዉ።  በቻይና ተቃዋሚ አልያም ተቀናቃኝ  ፓርቲ እንዲሁም ነፃ ፕሬስ የለም። የሲቪክ ማትበራትም እንዲሁ የሉም ።  በመሆኑም አሁን በተኅዋሲዉ የሚያዘዉም ሆነ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር በዉል በግልጽ አይታወቅም። እዉነታዉም ይደበቃል።

Coronavirus | China wird die Sperrung von Wuhan Coronavirus beenden
ምስል Getty Images/AFP/STR

በቻይና የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን በተመለከተ አንድ የጃፓን ብዙኃን መገናኛ በኹዋን የሚገኝ ሃኪምን ጠቅሶ እንደዘገበዉ፤ መንግሥት ይፋ የሚያደርገዉን ቁጥር ማመን አይቻልም።  የጃፓን የዜና ወኪል ኪዮዶ እንደዘገበዉ  በቻይና ታይሃን ውስጥ ከሚገኝ ገልተኛ የሕክምና ማእከል የመጣ አንድ ሐኪምን ጠቅሶ እንደገለፀዉ መንግሥት ይፋ የሚያደርገዉ ቁጥር ላይ እምነት አይጣልም፡፡

Coronavirus | China wird die Sperrung von Wuhan Coronavirus beenden
ምስል Getty Images/AFP/STR

ከሻንጋይ ቀጥሎ በቻይና አንድ ግዛት የኮረና ስርጭትን ለመግታት ያወጣዉን የአስቸኳይ ጊዜ ደረጃ ቁጥር ከአንድ ወደ ሁለት ቀንሷል፡፡ ይህ ማለት የኮሮና ስርጭትን በተመለከተ ከፍተኛው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  አሁንም በሌሎቹ አራት የቻይና ግዛቶች ዉስጥ ባሉ 33 ክልሎች አልያም ወረዳዎች  ተግባራዊ ነዉ። የተኅዋሲዉ ስርጭትን በተመለከተ ከሁባይ ግዛት ቀጥሎ በቤጂንግ እንዲሁም ቲያንዣን እና ሌሎች መዲና ቤጂንግ አዋሳኝ ላይ የሚገኙ  ከተሞች ዉስጥ ያለዉ ሁኔታ አይታወቅም። በሌላ በኩል የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራሮች የኤኮኖሚ እና የወታደራዊ ጉዳይ ተወካዮች በኮሮና ተኅዋሲ መለከፍ አለመለከፋቸዉ  የተነገረ  ነገር የለም።

ሆኖም የቻይና ግዛት እና የፓርቲ አመራሮች በተቻለ መጠን መዲና ቤጂንግ እና አካባቢዉን ከቫይረሱ ስርጭት ለመከላከል እየሞከሩ መሆናቸውን ያመላከታል። ይህ ደግሞ ወደ ቤጂንግ የሚበሩ ጥቂት ዓለም አቀፍ በረራዎች በዋና ከተማው ውስጥ ባሉት ሁለት የአየር ማረፍያዎች ማረፍ አይችሉም። እነዚህ ከዉጭ ሃገራት የሚገቡ አዉሮፕላኖች ቤዢንግ አቅራብያ በሚገኙ ግዛቶች ዉስጥ በሚገኙ  አዉሮፕላን ማረፍያዎች እንዲያርፉ ሆንዋል። ወደ ቻይና የሚገቡ ተጋዦች በሙሉ ከአዉሮፕላን እንደወረዱ ለ 14 ቀን ራሳቸዉን አግልለዉ የሚቀመጡበት እና ክትትል ወደሚደረግበት ሥፍራም ይወሰዳሉ።     

እንድያም ሆኖ አሁን የቻይና ብዙኃን መገናኛዎች ፊታቸዉን ወደ ዉጭ ሃገራት በተለይም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እና ወደ አዉሮጳ የመለሱ ይመስላል። እንደ በርካታ ቻይናዉያን እምነት የኮሮና ስርጭትን ለመግታት አዉሮጳና አሜሪካ የቻይናን ተሞክሮ  ተግባራዊ ማድረግን ይፈልጋሉ።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ