የህወሓት ኃይል ከአማራና ከአፋር ክልሎች እንዲወጣ ተጠየቀ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 28 2013ማስታወቂያ
ዮናይትድስቴትስ ፣ ህወሓት ወታደራዊ ኃይሉን ከአማራና አፋር ክሌሎች በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ጠየቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኛ በሰጡት መግለጫ የአማራ ክልላዊ መንግስትም ወታደራዊ ኃይሉን ከምዕራባዊ ትግራይ እንዲያስወጣ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የቀጠለው ውጊያ እንዳሳሰባቸው ገየገለጹት ፕራይስ የኤርትራ መንግስትም ወታደራዊ ኃይሉን ከኢትዮጵያ በዘላቂነት እንዲያስወጣ በድጋሚ ጠይቀዋል። ተፋላሚ ኃይሎች በድርድር ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረሰ መነጋገር እንዲጀምሩም አሳስበዋል።ከአትላንታ ጆርጅያ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል ።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ