የላፕሴት ፕሮጀክት እና የኬንያ ስጋት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2010ማስታወቂያ
ዘ ስታንዳርድ የተሰኘው የሀገሪቱ ዕለታዊ ጋዜጣ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ አሰብ ወደብ ማዞሯ ላፕሴት ፕሮጄክትን እና ኬንያ ገና እየገነባችው ያለውን በሕንድ ውቂያኖስ ዳርቻ የሚገኘውን ላሙ ወደብን ዋጋ ቢስ ያደርጋቸዋል፡፡ ጋዜጣው ባለሙያዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ስምምነት ኬንያ ላሙ ወደብን የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የገቢ እና ወጭ ንግድ ማዕከል ለማድረግ እና የሰሜናዊ ግዛቶቿን ለማልማት የያዘችውን መጠነ ሰፊ ዕቅድ ያኮላሸዋል የሚል ስር የሰደደ ስጋት አለ፡፡ ከናይሮቢ ቻላቸው ታደሰ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ቻላቸው ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ