1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሦስቱ የጀርመን መራሄ መንግሥት እጩዎች የመጀመርያ ክርክር መድረክ

ሰኞ፣ ነሐሴ 24 2013

አራት ሳምንታት ለቀረዉ ጀርመን የፓርላማ ምርጫ ትናንት የፓርቲ ከፍተኛ እጩዎች በቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት ቀርበዉ ጠብቀረሽ ክርክር አካሂደዋል። የክርስቲያን ዴሞክራቱ አርሚን ላሼት ፣ የሶሻል ዲሞክራቱ ኦላፍ ሾልዝ እና አረንጓዴ አናሌና ቤርቦክ እጩዎች በክርክራቸዉ የኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል ይደረጋል በሚባለዉ ጥረት ላይ ተስማምተዋል።

https://p.dw.com/p/3zgc3
Deutschland | Bundestagswahl Kanzlerkandidaten Triell | Laschet, Baerbock und Scholz
ምስል RTL/dpa/picture alliance

በአየር ንብረት ጥበቃና ግብርን በተመለከተ ጠንከር ያለ ክርክርን አካሂደዋል

አራት ሳምንታት ለቀረዉ ጀርመን የፓርላማ  ምርጫ ትናንት የፓርቲ ከፍተኛ እጩዎች በቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭት ቀርበዉ የፖለቲካ ምርህአቸዉን በማንሳት ጠብቀረሽ ክርክር አካሂደዋል። የክርስትያን ዲሞክራት ህብረት CDU / የክርስትያን ሶሻል ህብረት CSU ፣ ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ SPD እና የአረንጓዴ ፓርቲ Grüne የመራሄ ወይም የመራሂተ መንግሥት እጩዎች  ሁለት -ሰዓት በዘለቀዉ የቴሌቭዝን ክርክር ፣ በተለይም በአየር ንብረት ጥበቃ እና የግብር ፖለቲካን በተመለከተ ጠንከር ያለ ንግግርን ተለዋዉጠዋል። የክርስቲያን ዴሞክራቱ አርሚን ላሼት ፣ የሶሻል ዲሞክራቱ ኦላፍ ሾልዝ እና አረንጓዴ አናሌና ቤርቦክ እጩዎች  በክርክራቸዉ የኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል ይደረጋል በሚባለዉ ጥረት ላይ ተስማምተዋል። በዚህ መሠረት ሦስቱም ሎክ ዳዉን ወይም ሁሉን ነገር ከመዘጋጋት የክትባቱን መጠን ለመጨመር ይፈልጋሉ። የፊታችን መስከረም 16፤ 2013 ዓም በጀርመን የምክር ቤትምርቻ ይካሄዳል።  

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ