1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰኔ 25 ቀን፣ 2010 ዓም ስፖርት

ሰኞ፣ ሰኔ 25 2010

በሩስያ ወደ ሁለተኛው ዙር  የተሸጋገረው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ገና በጅማሮው ገናና የሆኑ ታዋቂ ቡድኖችን እያሰናበተ ግስጋሴውን ቀጥሏል። የ2014 ዓም የዓለም ዋንጫ ባለቤት የነበሩት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በወረደው የቡድናቸው አቋም ሰበብ ሽንፈት ደርሶባቸው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

https://p.dw.com/p/30g7L
Paris Diamond league 2018
ምስል DW/H. Tiruneh

ስፖርት ፤የሰኔ 25 ቀን፣ 2010 ዓም

የዓለም ኮከቦች በመባል በየግላቸው አምስት አምስት ጊዜ የወርቅ ኳሱን የተሸለሙት ፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና አርጀንቲንያዊው ሌዎኔል ሜሲ የአገሮቻቸውን ብሔራዊ ቡድኖች በሩስያው የዓለም ዋንጫ ግጥሚያ ማቆየት ሳይሳካላቸው ቀርተዋል። አስተናጋጅ ሩስያ ስጳኝን በመርታት ወደ 2ኛው ዙር አልፋለች። አፍሪቃ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ካሳተፈቻቸው አምስት ቡድኖች አንዱም ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለም። አህጉሩ ይህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመው ከ36 ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። በፓሪስ የዳይመንድ ሊግ አትሌቲክስ ውድድር፣ በኦስትርያ ደግሞ ትናንት የፎርሙላ ዋን የመኪና እሽቅድምድም ተካሂደዋል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ