የሰኞ መስከረም፤ 7 ፤ 2011 ዓ.ም የስፖርት ዝግጅት
ሰኞ፣ መስከረም 7 2011አትሌቲክስ
በበርሊን በተደረገው የ 45 ኛ ው የ «BMW» በርሊን ማራቶን ውድድር ኬንይዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጊ 2፥01፥39 በመግባት ኣዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግብዋል።ኪፕሮቶ 2:06:23 እንዲሁም ሊላው ኪንያዊ ዊልሶን ኪፕሳጎን 2:06:48 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ በማውጣት አሽንፍዋል።
የ 33 ዓመቱ ኪንያዊዊ አትሌት ኪቾጊ ከውድድሩ በኋላ የተሰማኝን ደስታ ለመግላፅ ቃላት ያጥረኛል የዓለምአዲስ ከብረወሰንን በማስመዝገቤ ታላቅ ክብር እና ደስታ ይሰማኛል ሲል ደስታውን ገልፅዋል። የወንዶች የማራቶን ውድድር የመግቢያ ሰዓት ለ 6ኛ ግዜ መሻሻሉ ነው።በተመሳሳይ የበርሊን ሴቶች ማራቶን ውድድር ኪንያዊትዋ ግላድየስ ቺሪኖ ሁለት ሰአት ከእስራ ስምንት ደቂቃ ከእስራ እንድ ሰከንድ በመግባት አሽናፊ ሁናለች። በ 45ኛው የ «BMW» የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሊቶች ሩት አጋ እና ጥሩነሽ ዲባባ 2፥18፥34 እና 2፥18፥55 በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል።
ቺሪኖ የበበርሊን ዘንድሮ የተካሄደዉን የማራቶን ዉድድር ጨምሮ በ 2015 እንዲሁም ያለፈው ዓመት 2017 በማሸናፍ ለ 3ኛ ግዚ የበርሊን ማራቶን ክብር አግኛታለች።
እግር ኩዋስ
በዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ምክንያት እረፍት የሰነበተው ሀገራት ክለቦች የእግር ኩዋስ ጨዋታ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ተጀምሮዋል። በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ በ አምስተኛው የጨዋታ ቀን ቅዳሜ እለት በዊንብሊ ስታድየም ሊቨርፑልን ያሰተናገዱት ቶትንሀሞች በየርገን ክሎፕ ቡድን 2 ለ 1 ተረተዋል። ቦርማውዝ ቀበሮዋችን 4 ለ 2 በመርታት ወደመጡ በት መልሶዋቸዋል።
ቸልሲ ካርዲፍን 4ለ 1 አሽንፎዋል። ጎሎቹም በፍፁም ቅጣትምት የተገኝውን ጨምሮ ኤድን ሀዛርድ 3 ጎሎችን ሲያገባ፤ ዊልያን አራተኛውን ጎል አስመዝግብዋል።
ሀደርስ ፊልድ በሜዳው በ ክርስታል ፓላስ 1ለ 0 ተረትዋል።
ፍርልሀምን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ሳኒ፥ሲልቫ፥እና እስተርሊን ባስቆጠሩት ጎሎች 3ለ 0 ፉልሃምን ረትዋል። ወደ ኒው ኣስትል ያቀናው አርሰናል ኒው ካስልን 2ለ 1 ረትዋል
ማንችስትር ዩናይትድ ቡድናቸውን ይዘው ወደዋትፈርድ የተጉዋዙት አሰልጣኝ ጆሲ ሞሪኖ አንድ ተጫዋቻቸውን በቀይ ከሚዳ አጥተው 3 ለ 1 አሸንፈው ሦስት ነጥብ ይዘው ተመልሰዋል ፥ ዎልቭስ በርሊን ሁለት ለዚሮ ኤቨርተን በ ዊስት ሀም ሦስት ለአንድ ተረትዋል ዛሪ ሳውዝ ሀምፕተን ክቭብራይተን ይጫወታል።
ሃና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ