የጳጉሜ 5 ፣2010 የስፖርት ዝግጅት
ሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2010ማስታወቂያ
ዛሬ የምንሰናበተው የ2010 ዓም የመጨረሻው የስፖርት ዝግጅታችን፣ የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች በተለይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ውጤትን አካቷል። የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ በካሜሩን አስተናጋጅነት በተለያዩ የአፍሪቃ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከሴራልዮን ቡድን ጋር የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦስት ነጥብ ይዞ ቢወጣም ከምድቡ የመጨረሻውን ደረጃ ይዟል። ከዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ አትሌት ሰሎሞን በርጋ ጋርም በስፖርት ዝግጅታችን አጭር ቆይታ እናደርጋለን። ስለሜዳ ቴኒስም የተዘናቀረ ዘገባ አለን ሙሉ ዝግጅቱን የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ታቀርባዋለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሒሩት መለሰ