1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መግለጫ

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2007

ቡድኑ እስከ ዛሬ ተዘዋውሮ በጎበኛቸው አካባቢዎች ያነጋገራቸው ተወዳዳሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ምርጫው ነፃ እና አሳታፊ እንዲሆን ምርጫ ቦርድ ሁሉንም ወገን እንዲያወያይ መጠየቃቸውን የቡድኑ መሪ የቀድሞው ናሚብያ ፕሬዝዳንት ሂሲኬ ፑኜ ፑሃማባ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/1FTM2
Äthiopien Wahlen 2015
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

በመጪው እሁድ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የሚታዘበው የአፍሪቃ ህብረት ቡድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጣለበትን ሙያዊ ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ጠየቀ። ቡድኑ እስከ ዛሬ ተዘዋውሮ በጎበኛቸው አካባቢዎች ያነጋገራቸው ተወዳዳሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ምርጫው ነፃ እና አሳታፊ እንዲሆን ምርጫ ቦርድ ሁሉንም ወገን እንዲያወያይ መጠየቃቸውን የቡድኑ መሪ የቀድሞው የናሚብያ ፕሬዝዳንት ሂፍከንፑንየ ፎአምባ አስታውቀዋል ። እነዚሁ ወገኖች ከኢትዮጵያ ፕሬስ ህግ ከፀረ ሽብር ህግና ከሲቪል ማህበረሰብ ህግ የተወሰኑት ክፍሎች የዜጎችን በፖለቲካ እንቅስቃሴዎች የመሳተፍ መብትን የሚገድቡ ናቸው ሲሉ ስጋታቸውን ለታዛቢዎች መግለፃቸውን የታዛቢው ቡድን መሪ ተናግረዋል ። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ