የኢትዮጵያና ኤርትራ የጦርነት ሥጋት
ዓርብ፣ ሰኔ 17 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያና ኤርትራ አዋሳኝ ድንበር የሠፈረዉ የሁለቱ ሐገራት ጦር በቅርቡ ፆረና በተባለዉ ግንባር ከተጋጨ ወዲሕ ሁለቱ ሐገራት ዳግም ሙሉ ጦርነት ይገጥማሉ የሚለዉ ሥጋት፤ ጦርነት እንዳይገጥሙ የሚሰጠዉ ምክርና ማስጠንቀቂያም እንደቀጠለ ነዉ።የሁለቱ መንግስታት ወታደራዊ ዝግጅት እና የቃላት እንኪያ ሰላንቲያ ግን እስካሁን አላቋረጠም።አንደሚሉት በድንበር አካባቢ የሠፈረዉ ሕዝብ ከአካባቢዉ እንዲለቅ መታዘዙን የሚጠቁሙ ምንጮችም አሉ።የአዲሰ አበባዉ ዘጋቢያችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የፖለቲካ ጉዳይ ጋዜጠኞች እንደሚሉት ግን ሁለቱ ሐገራት አሁን ባሉበት ደረጃ ሙሉ ጦርነት መግጠም አይችሉም።ዝርዝሩን እነሆ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ