1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት

እሑድ፣ ሰኔ 19 2008

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለረጅም ጊዜ ጋብ ያለ ይመስል የነበረዉን የድንበር ላይ ግጭት እንደገና የጀመሩ ይመስላል። ሰኔ አምስት በተለይ ጾረና በተባለዉ ግንባር የሁለቱ ሃገራት ጦር ተጋጭተው ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ኃይል ከሁለቱም ወገን መገደሉና መቁሰሉ ተዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/1JDpO
Karte Äthiopien Eritrea Grenze Amharisch

የኢትዮ-ኤርትራ ዉዝግብና ግጭት

ሁለቱ ሃገራት የድንበር ላይ ጦርነትን ካቆሙ ከ1992 ዓ,ም ወዲህ ከተካሄዱት ግጭቶች ያሁኑ ከባዱ ነዉ ተብሎአል። የአሁኑን ግጭት ቀድሞ የጀመረዉ ወገን በግልፅ አልታወቀም። የአስመራና የአዲስ አበባ መንግሥታት ግን በግጭቱ መጀመር እርስ በርስ እየተወቃቀሱ ነዉ። ከሰኔ 5ቱ ግጭት በኋላ በድንበር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች ይዘግባሉ።

የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ለተመድ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተመልካች ም/ቤት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ኤርትራን ለመዉረር እየተዘጋጀች ነዉ በማለት ወቅሰዋል። የተመድ እና ዩኤስ አሜሪካ ሁለቱ ሃገሮች ወደ ጦርነት እንዳይገቡና ነገሮች እንዳይባባሱ በትዕግስት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። እስካሁን በድንበር አካባቢ ያለዉ ዉጥረት እየተባባሰ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች ይናገራሉ። ዉጥረት ስላጠላበት የኢትዮጵያ ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወያዩልን የጋበዝናቸዉ፤ መቀመጫዉን አዲስ አበባ ያደረገዉ ዓለማቀፍ የምክክርና የጥናት የትብብር ማዕከል ባልደረባ አምሳደር ተፈራ ሻዉል፤ በኢትዮጵያ ኤርትራ ጉዳይን በቅርበት የሚያዉቁት በለንደን ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊ አቶ አሉላ አብርሃ እንዲሁም ነኖርዌ ነዋሪ የሆኑት የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲን ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ