የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሃሳብና ያስከተለው ውይይት
ሐሙስ፣ ጥር 8 2006ማስታወቂያ
በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰለም ለማስፈን ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካን አምባሳደር ዴቪድ ሺን በሰነዘሩት ሃሳብ ላይ ለዶቼቬለ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል ። አስተያየት ሰጭዎቹ የሁለቱ ሃገራት የሰላም ውይይት ህዝባዊ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባ ከማሳሰብ አንስቶ መሠረታዊ የስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል ። ዶቼቬለ የኤርትራን መንግሥት ሃሳብ ለማካተት ያደረገው ጥረት ግን አልተሳካም። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ያቀርብልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሃመድ