1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራውያን ጉባኤ በብራስልስ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2011

ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ካወረዱም በኋላ የኤርትራ ወጣቶች ስደት አለመቆሙ ተገለጸ። ይህ የተነገረው ብራስልስ ላይ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እና ዓርብ «የአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እና የኤርትራ ሕዝብ የወደፊት ደህንነት» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/3AGcM
Eritrea Straßenszene in Asmara
ምስል Reuters/T. Mukoya

«ዛሬም የተሰዳጆች ቁጥር አልቀነሰም»

የስብሰባው አዘጋጆች የአውሮጳ የውጭ ፖሊሲ አማካሪዎች የሚባል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና ሌሎች የተለያዩ የኤርትራውያን ስብስቦች ናቸው ተብሏል።  ከኬንያ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከእስራኤል ከካናዳ እና ከበርካታ የአውሮጳ አገሮች የመጡ ኤርትራውያን ምሁራን እና ባለሙያዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችም በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ከብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።  

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ