የኤርትራ ማዕድን አዉጪ ኩባንያ ክስ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2010ማስታወቂያ
ቢሻ በተባለዉ የኤርትራ ማዕድን ማዉጪያ ሥፍራ ተፈፅሟል የተባለዉን በደል የካናዳ ፍርድ ቤት እንዲመረምር ተወሰነ።ኤርትራ ዉስጥ ማዕድን የሚያወጣዉ ነብሱን የተባለ የካናዳ የማዕድን ኩባንያ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር አስገድዶ በዝብዞናል የሚሉ ስድት ኤርትራዉያን ኩባንያዉን ከሰዋል።ኩባንያዉ ተፈፀመ የተባለዉ በደል ተፈፅሞ ከሆነ የተፈፀመዉ ኤርትራ ዉስጥ በመሆኑ ክሱም መመስረት ያለበት ኤርትራ ዉስጥ ብሎ ሲከራከር ነበር።ይሁንና የካናዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ በካናዳ ፍርድ ቤት እንዲታይ በይኗል።የቶሮንቶዉ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ታሪኩን ተከታትሎታል።
አክመል ነጋሽ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ