1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ፕሬዚደንት የሰጡት ቃለ መጠይቅ

ሰኞ፣ ጥቅምት 26 2011

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየተሻሻለ የመጣው ግንኙነት ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መልካም አጋጣሚ ይዞ የመጣ መሆኑ የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ተናገሩ።፡ ፕሬዚዳንቱ ከሀገራቸው ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ በርከት ያሉ ዓለምአቀፋዊ፣ አካባቢያዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን አንስተው ማብራርያ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/37gjr
Isayas Afewerki
ምስል Imago/photothek/U. Grabowsky

የኤርትራ ፕሬዚደንት የሰጡት ቃለ መጠይቅ

የአልጀርስ የድንበር ውሳኔ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቶ የነበረው በውጭ ኃይሎች ጫና እንደነበር የገለፁት ፕሬዝዳንት ኢስይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ አሁን በተፈጠረው ለውጥ፣ በኤርትራ ህዝብ ትግልና ፅናት ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ብለዋል። "የባድመ ችግር ፈጠራ ነው። በሁሉም ሁኔታ ቢታይ ምንም ዓይነት የድንበር ችግር አልነበረም። የድንበር ችግር ቢኖርም በተለያየ መንገድ መፍታት ይቻል ነበር" ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ  "ውሳኔው ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው በወያነ ስርዓት ሳይሆን፡ በዚያን ጊዜ በነበሩ የዋሽንግተን አስተዳደሮች እንጂ" ሲሉ ተናግረዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ግንኙነቱ አሁን በተሻለና ተስፋ በሚሰጥ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።፡ በኤርትራ ፕሬዚዳንት ቃለ መጠይቅ በርከት ያሉ አስታያየቶች እየተሰጡበት ነው።

Karte Äthiopien Eritrea Grenze Amharisch

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተስፋለም ወልደየስ