የከባድ መኪና ሾፌሮች ሮሮ
ዓርብ፣ ሰኔ 10 2014ማስታወቂያ
ከ እና ወደ ጅቡቲ ወደብ የወጪና ገቢ ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ከአዋሽ ደወሌ እና ከአዋሽ ሚሌ ባሉ መንገዶች «ያልተገባ» ያሉትን ገንዘብ እንዲከፍሉ መገደዳቸዉን አስታወቁ።ሾፌሮቹ እንደሚሉት በተለይ በሶማሌ ክልል በሚገኙ ከተሞችና ኬላዎች የፖሊስና የልዩ ኃይል ባልደረቦችነን የሚሉ ታጣቂዎች የሾፌሮቹን ገንዘብ፣ ተንቀሳቃሽና ስልክና አልባሳት ጭምር ይዘርፋሉ።በሶማሌ ክልል «ሲቲ ዞን» የተባለዉ አስተዳደር ግን ከሾፌሮቹ የደረሰዉ አቤቱታ እንደሌለ አስታዉቋል።ይሁንና ጉዳዩን ለመከታተል ቃል ገብቷል።
መሳይ ተክሉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ