የድንበር አለመከፈት የፈጠረው ቅሬታ
ሐሙስ፣ ኅዳር 20 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ማውረዳቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኙ መንገዶችን እና ድንበሮችን መክፈታቸው ይታወሳል። ሆኖም በሁመራ አካባቢ ያለው ድንበር እስካሁን አለመከፈቱ በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ድንበሩ ያልተከፈተው የኤርትራ መንግስት ባለመፈቀዱ ነው ይላሉ፡፡ ውይይት ተደርጎ የድንበር መንገዱ በቅርቡ ይከፈታል ብለው እንደሚጠብቁም ይናገራሉ፡፡
የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ድንበሩ እንዲከፈት ከመጀመርያው ጀምሮ ፍላጎት እንደነበር በመግለፅ እየተደረገ ባለው ንግግር በቀጣይነት ይከፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
በሑመራ ኦምሓጀር በኩል ያለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በተከዘ ወንዝ የሚለያይ ሲሆን፣ ቀደም ብሎ የተሰራ ድልድይ ሁለቱን ሀገራት ያገናኛል፡፡
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ተስፋለም ወልደየስ
ኂሩት መለሰ