1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የጦር ኃይል በጀትና የጦር መሣሪያ ድጋፍ

ሰኞ፣ የካቲት 21 2014

ጀርመን ከዚህ ቀደም የነበረውን የጦር መሣሪያ ደንቧን ወደጎን ብላ በሳምንቱ መጨረሻ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልካለች። የራሷንም የጦር ኃይል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መዘዝ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጠናከር 100 ቢሊየን ዩሮ መመደቧን ይፋ አደረገች።

https://p.dw.com/p/47jQe
Deutschland | Soldaten mit Panzerfaust
ምስል Sebastian Gollnow/dpa/picture alliance

ጀርመን ለዩክሬንም የጦር መሣሪያ ረድታለች

የዩክሬን ወታሮች ወደ ዋና ከተማ ኪየቭ የሚገሰግሰውን የሩሲን የጦር ኃይል ለመመከት እየታገሉ መሆኑ እየተነገረ ነው። ዩክሬን በአንድ በኩል እየመከተች በሌላ ወገን ከሩሲያ ጋር ለመደራደር የሁለቱም ሃገራት ልዑካን ዛሬ ተገናኝተው ውይይት መጀመራቸውን ዘገባዎች ያሳያሉ። የተፈራው የሁለቱ ሃገራት ፍጥጫ ወደ ጦርነት ከተሸጋገረ ወዲህም ምዕራባውያን ሃገራት ለዩክሬን ድጋፍ ለመስጠት የየበኩላቸው እያደረጉ ነው። ጀርመን ከዚህ ቀደም የነበረውን የጦር መሣሪያ ደንቧን ወደጎን ብላ በሳምንቱ መጨረሻ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልካለች። የራሷንም የጦር ኃይል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መዘዝ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጠናከር 100 ቢሊየን ዩሮ መመደቧም ተነግሯል። ሩሲያ በበኩሏ ሁሉም የኒኩሊየር ጦር መሣሪያዎቿ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጥታለች። ከሩሲያ ጋር የተሻለ ቅርርብ እንዳላቸው የሚነገረው የጀርመን ፖለቲከኞች ጦርነቱ እንዳይስፋፋ የሚኖራቸው ሚና ምን ያህል ይሆን? የበርሊን ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን አነጋግረነዋል። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል 

ሸዋዬ ለገሠ 

እሸቴ በቀለ