1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኖች ባህላዊ የገና ገበያ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2014

የተለያዩ የጀርመን ከተሞች የገና በአልን ለመቀበል ሽርጉድ እያሉ ነው። ዶይ ቸቬ የሚገኝባት ጥንታዊታ የቦን ከተማም በገና ዛፎችና መብራቶቸ ተሽቆጥቁጣ ማየት አንዳች ሐሴትን ይፈጥራል። በከትተማዋ እምብርት በአመት አንዴ የሚቆመው የገና ገበያ ማእከል የበአሉን ድባብ ከወዲሁ አድምቆታል።

https://p.dw.com/p/44OQr
Check-in | Sendung vom 18.12.2021
ምስል DW

ገናን ለመቀበል ሽርጉዱ ቀጥሏል

የተለያዩ የጀርመን ከተሞች የገና በአልን ለመቀበል ሽርጉድ እያሉ ነው። ዶቸቨለ የሚገኝባት ጥንታዊታ የቦን ከተማም በገና ዛፎችና መብራቶቸ ተሽቆጥቁጣ ማየት አንዳች ሃሴትን ይፈጥራል። 

በከትተማዋ እምብርት በአመት አንዴ የሚቆመው የገና ገበያ ማእከል የበአሉን ድባብ ከወዲሁ አድምቆታል። በእንጨት በጊዚያዊነት የተስሩ ሱቆች ባህላዊን የቤት አሰራር ተከትለው በእንጭት የተገነቡ ሲሆን በገና ዛፎች፣ ብተለያዩ ህብረቀለማት ባሸበረቁ መብራቶች ደምቀው ለታዳሚዎች  የገና ስጦታዎች፣ የተለያዩ ሽቀጦችንና ምግቦች ለገበያ ይቀርባሉ።

በተለይ በአመት አንዴ ለገበያ የሚቅርበ ግሉቫይን ወይም ደግሞ የሞቀ የወይን ጠጅ ታዳሚዎች በፍቅር የሚያዘወትሩት ባህላዊ መጠጥ  ነው። አምና በኮረና ምክንያት መሰባሰቡ ተከልክሎ ሰለነበር ዘንድሮ ክትባት ለወሰዱት ክፍት በመሆኑ በየምሽቱ የገበያ ማእክሉ ደምቆ ይታያል።

ኤርትራዊው ዳንአል ሙሴ በገና ገበያ ሲታደም ለመጀመርያ ጊዜው ነው። በገበያው በርካታ እቃዎች በተለይም ለገና ስጦታ የሚውሉ  አንድቦታ ላይ ማግኝት እና ስነስር አቱን ማየት ክፍተኛ ደስታ እንደሰጠው አጫውቶናል። እንደጀርመኖቹ ሁሉ ሙቅ የወንጠጅም ተጎንጭቶ ከግደኞቹጋ እየተዝናና እንደሆነ አጫውቶናል።

ከ20 አመታት በላይ በጀርመን የኖረው በቢግዚ የጀርመን ኑሮውን ከሚያደምቁለት አንዱ ባህላዊው የገና ገበያ እንደሆነ አጫውቶናል። የተለያየ አገራት ምግቦች እየተመገቡ ከቤተሰብ ጋ ማሳለፍ በጣም ያስደስተኛል ብሎናል።

ጁልያና በርገርም ከገበያ ማእከሉ ታዳሚዎች ነበሩ። እነሱ እንደነገሩን በኮረና ምክንያት አምና መከልከሉ ድብርት ጭሮባቸው የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ክትባት ለውሰዱ ነዋሪዎች ክፍት በመሆኑ ባመት አንዴ የሚቀርበውን የሞቀ የወይን ጠጅ እየጠጡ ከወዳጅ ዘመድ ማሳለፋቸው እንዳስደሰታስቸው ነግረውናል። ባህላዊው የገና ገበያ እስከ ገና በአል ድረስ ይቀጥላል።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ