1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅቡቲ ኤርትራ የድንበር ዉዝግብና የአፍሪቃ ኅብረት ዉሳኔ 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 27 2009

በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል ዉዝግቡ በተካረረበት በዚህ ወቅት የአፍሪቃ ኅብረት ወደ አስመራ ልዑካኑን እንደሚልክ ዛሬ አስታወቀ። ኅብረቱ ለቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እና ለቀድሞዉ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ኑክሩማ ሐዉልት ለማቆም በሙሉ ድምፅ ወስኖአል።

https://p.dw.com/p/2fvX9
Afrikanische Union Marokko nach 33 Jahren wieder aufgenommen
ምስል picture alliance/AA/Minasse Wondimu Hailu

NEU Q & A_AU-Gipfe_Streit ZW Eritrea & Djibouti /Jugendarbeitslosigkeit/Statu - MP3-Stereo



ማክሰኞ ከቀትር በኋላ የተጠናቀቀዉ 29ኛዉ የአፍሪቃ ኋብረት የመሪዎች ጉባኤ የኅብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂ መሃማት እንዳመለከቱት የኤርትራ ወታደሮች አወዛጋቢዉን የራስ ዱሜራ ተራራ አካባቢ ወርረዋል ስትል ጅቡቲ ክስ ወዳቀረበችባት ኤርትራ መልዕክተኞችን እንደሚልኩ መናገራቸዉን ቦታዉ ላይ የተገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ በስልክ ነግሮናል። ኅብረቱ በተጨማሪ ከተነጋገረባቸዉ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል በተለይ በአህጉሪቱ ለሚገኘዉ ወጣት ሥራ አጦች የሥራ እድልን መፍጠር እና፤ ኅብረቱ የሚንቀሳቀስበት የፊናንስ ጉዳይ ነበሩ። በሌላ በኩል ለቀዳማዊ ኃይለስላሴ እና ለቀድሞዉ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ኑክሩማ ኃዉልት ለማቆም ኅብረቱ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን ቦታዉ ላይ የነበረዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን በስልክ ነግሮናል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ 


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ