1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅቡቲ እና የኤርትራ ውዝግብ

ረቡዕ፣ ሰኔ 14 2009

ጅቡቲና ኤርትራ በድንበር ግዛት ይገባኛል ጥያቄ በሚወዛገቡበት በጋራ ድንበራቸው  በሚገኘው የራስ ዱሜራ አካባቢ ካታር አስፍራው የነበረውን ሰላም አስከባሪ ጦሯን ካስወጣች በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረቱ እንዳዲስ ተካርሯል። የካታር ጦር መውጣትን ተከትሎ ኤርትራ ወታደሮቿን በአወዛጋቢው ግዛት  አስፍራለች።

https://p.dw.com/p/2f7ea
Karte Dschibuti und Nachbarländer
ምስል AP

Ber.Washington DC(Eritrea-Djibouti Strei UNSC) - MP3-Stereo

ይህም ተገቢ አይደለም ስትል ጅቡቲ ለተመድ እና ለአፍሪቃ ህብረት አቤት ብላለች። ይህንኑ ውዝግብ በተመለከተ ከጅቡቲና ከኤርትራ መረጃ እንደደረሰው ያስታወቀው የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት በጉዳዩ ላይ መክሮ ሁለቱ ሀገራት ውዝግቡን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

መክብብ ሸዋ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ