1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የፕረስ ነፃነት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2009

ዛሬ በመላዉ ዓለም ታስቦ የዋለዉን የፕረስ ቀን ምክንያት በማድረግ የተሠራጩ መልዕክቶች እንዳረጋገጡት ከዩናይትድ ስቴትስ እስከ ቱርክ በሚገኙ ሐገራት የፕረስ ነፃነት እየተደፈለቀ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2cJ5q
Pressefreiheit
ምስል picture-alliance/ZB/B. Pedersen

Beri Berlin (WPFD-Dawit Issak) - MP3-Stereo

 

የፕረስ ነፃነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መምጣቱን የተለያዩ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት እና የፕረስ ነፃነት ተሟጋቾች አስታወቁ። ዛሬ በመላዉ ዓለም ታስቦ የዋለዉን የፕረስ ቀን ምክንያት በማድረግ የተሠራጩ መልዕክቶች እንዳረጋገጡት ከዩናይትድ ስቴትስ እስከ ቱርክ በሚገኙ ሐገራት የፕረስ ነፃነት እየተደፈለቀ ነዉ። የብዙ ሐገራት ጋዜጠኞች ሥራቸዉን እንዳያከናዉኑ ይዋከባሉ፤ ይታሰራሉ፤ ይገደላሉም። የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) በበኩሉ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ እንደ ጎርጎሪያዉያኑ አቆጣጠር ከ2001 ጀምሮ የታሠረዉን ኤርትራዊ-ሲዊድናዊዉ ጋዜጠኛን ሸልሟል።  በተመድ የኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ልዩ ዘጋቢ ሼይላ ኬታሩት የአስመራ ባለስልጣናት ዳዊት ይስሐቅን እና ሌሎች በሕገ ወጥ መንገድ ይዘዋቸዋል ያሏቸውን ሰዎች መንግሥት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ዛሬ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት በምህጻሩ ዩኔስኮ የ2017 ዓምን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ተሸላሚው የ52 ዓመቱ ኤርትራዊ ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ከታሰረ 16 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ይቀራሉ። ኤርትራ ነፃነትዋን ባወጀች በዓመቱ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ዳዊት ሰቲት ከተባለው የግል ጋዜጣ መሥራቾች አንዱ ነበር።የበርሊን ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ