ያለአግባብ የጫኑትን ነዳጅ ደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ መኪኖች በአፋር ክልል ተያዙ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2017ያለአግባብ ነዳጅ ደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ ነጃጂ ጫኝ መኪኖች በአፋር ክልል ተያዙ
በወሩ መጨረሻ ላይ የነዳጂ ዋጋ ክለሳ ይደረጋል በሚል ዕሳቤ በአፋር ክልል የተለያዮ ቦታዎች ነዳጅ ጭነዉ ተደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ ቦቴ መኪኖች ከተደበቁበት መያዛቸዉን የአፋር ክልል ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታዉቋል የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱልቃድር በጋላፊ ፣ ዉሀ ልማት ፣ ዲሽኦቶ: ፣ ሰርዶና ሌሎች ቦታዎች ነዉ ወደሀገር ዉስጥ ከገቡ ቀናትን ያስቆጠሩ ነዳጂ ጫኝ መኪኖች ማያዛቸውን ተናግረዋል።
የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የነዳጂ ጫኝ መኪናን ያሽከረከሩና ለስራቸዉ ደህንነት ሲባል ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ አስተያየት ሰጭ በጅቡቲ ነዳጂ ለመቅዳት በሚኖር ወረፋ ከአስር እስከ አስራአምስት ቀናትን በዚያ ብንቆይም የነዳጂ ጫኝ መኪና ያሏቸዉ ባለማድያዎች ግን በወሩ መጨረሻ ላይ ነጃጂ የጫኑ መኪኖቻቸዉ እንዲዘገዮ መፈለጋቸውን ገልጸዋል።
ነዳጂን ከጂብቲ በማስመጣት ለተጠቃሚዎች የሚያከፋፋሉት የነዳጂ ማድያ ስራአስኪያጂ የሆኑት አቶ ታደለ በቀለ ችግሩ ባለማደያዎች ዋጋ ለመጨመር በሚያደርጉት ጥረት ሳይሆን የአቅርቦት እጥረት በመኖሩ የተፈጠረ ነዉ ባይ ናቸው።
በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታሪፍ ጭማሪ እና የነዋሪው አቤቱታ
ከሰሞኑ በአፋር ክልል በነጃጂ ጫኝ ቦቴ መኪኖች ላይ እየተደረገ ያለዉ ክትትል እስከምንድረስ ነዉ ብለን የጠየቅናቸዉ የየክልሉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱል ቃድር መኪኖቹ የደህንነት ስጋት ሳይገጥማቸዉ ከክልሉ እንዲወጡ የማድረግ ተግባር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም ነዳጂ የጫኑ ቦቴ መኪኖች በአፋር ክልል ተደብቀዉ እንዳይቆዮ ከተለያዮ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመሆን ይሰራል ተብሏል።
ኢሳያስ ገላው
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ