ድጋፍ የሚሹት ከሆሮጉድሩ ወለጋ የተፈናቀሉት ወገኖች
ሰኞ፣ መጋቢት 27 2013ማስታወቂያ
ከኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች በማንነታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመፍራት በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ከመንግሥት ተገቢው ድጋፍ እየተደረገልን አይደለም ሲሉ አመለከቱ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት እስካሁን የአካባቢው ነዋሪ በሚያደርግላቸው ድጋፍ ነው ኑሯቸውን ለመግፋት የተገደዱት። በተጠቀሰው አካባቢ ከአንድ ኂህ የሚበልጡ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ያመለከቱት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ልማት ባልደረባ በበኩላቸው ከመንግሥት ለተፈናቃዮቹ የተደረገው በቂ አይደለም ይላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ትናንት በዚሁ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ደንጎሮ እና ቢላ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዞኑ አስተዳደር አመልክተዋል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ