1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን እና ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬኑ ውዝግብ

ሰኞ፣ ጥር 30 2014

አዲሱ የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከዮክሬን ቀውስ ጋር በተያያዘ ከዩናይትድ ስቴትስ ኘሬዝደንት ጆሴፍ ባይደን ጋር እንደሚወያዩ እየተጠበቀ ነው። የመጀመሪያ የአሜሪካ ጉብኝታቸውንም ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/46dvw
Bundeskanzler Olaf Scholz
ምስል Michael Sohn/AP/picture alliance

የጀርመን መራሄ መንግሥት በአሜሪካ

አዲሱ የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከዮክሬን ቀውስ ጋር በተያያዘ ከዩናይትድ ስቴትስ ኘሬዝደንት ጆሴፍ ባይደን ጋር ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ። በቅርቡ ወደ ሥልጣን የመጡት የጀመርን መራሄ መንግሥት በአሜሪካ የመጀመሪያ ይፋ ጉብኝታቸውንም ጀምረዋል። በዚሁ ጉብኝታቸው ጀርመን ከዮክሬን ቀውስ ጋር በተገናኘ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሌሎች የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ኔቶ አጋሮቿ ጎን እንደምትሰለፍ መተማመኛ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ