ጠ/ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና ኤርትራ
ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2005ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ውይይት ለማካሄድ እንደምትፈልግ አስታወቀች ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ለአልጀዚራ ጣቢያ በሰጡትና የፊታችን ቅዳሜ በሚተላለፍ ቃለ ምልልስ ላይ መናገራቸው በተለያዩ ድረ ገፆች ላይ ተዘግቧል ። አቶ ኃይለማርያም ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብ በድርድር እንዲፈታ በተለያዩ ጊዜያት መጠየቃቸውን አስታውሰዋል ። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋራ ማካሄድ ስለምትፈልገው ውይይት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲን አነጋግረናል ። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ማካሄድ እፈልጋለሁ ስላለችው ውይይት የኤርትራን መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ሞክረን አልተሳካም።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ