1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሶስት ቀናት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2010

አቶ ፍጹም የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት እና ግንኙነት እንደሚያጠናክር ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ካደረገችው ደም አፋሳሽ ጦርነት እና ጦርነቱን ከተከተለው ፍጥጫ በኋላ ለጉብኝት ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ይኸ የመጀመሪያቸው ነው።

https://p.dw.com/p/31No6
Eritrea Präsident Isaias Afwerki
ምስል Eritrea Minister of Information/Y.G. Meskel

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሶስት ቀናት ጉብኝት አዲስ አበባ ይገባሉ። ኢሳያስ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ከጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ በቀረበላቸው ግብዣ መሆኑን አቶ ፍጹም አረጋ አረጋግጠዋል። አቶ ፍጹም የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት እና ግንኙነት እንደሚያጠናክር ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ካደረገችው ደም አፋሳሽ ጦርነት እና ጦርነቱን ከተከተለው ፍጥጫ በኋላ ለጉብኝት ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ ይኸ የመጀመሪያቸው ነው። የ72 አመቱ ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ጉብኝት በሚሊኒየም አዳራሽ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸውን አስከትለው ኤርትራን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ