16ኛው ታላቁ ሩጫ
እሑድ፣ ኅዳር 11 2009ማስታወቂያ
በውድድሩም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እና ከመዲናዋ የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ተካፍለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ገቢራዊ ካደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተሳተፈበት የአደባባይ ውድድር በሰላም መጠናቀቁን የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል። በአትሌቶች ምድብ የተካሔደውን ውድድር በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻሁን ከአማራ ማረሚያ ቤት አንደኛ፤ኬንያዊው ጆሩም ሉምባሲ ሁለተኛ እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊሱ አዱኛ ታከለ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በሴቶች ጎራ ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ ስፖርት ክለብ አንደኛ፤ሙልዬ ደቀቦ ከኦሮሚያ ፖሊስ ሁለተኛ እንዲሁም ታደለች በዳሶ ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ሶስተኛ በመውጣት አጠናቀዋል። የታላቅ ሩጫ አዘጋጅ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አዲስ አበባ ለአትሌቶች አትመችም ያልኩትን ሀሳብ የዛሬው ሩጫ አስመስክሮልኛል ይላል። ለዚህም ምክንያቱ አሸናፊዎች ከክልል የመጡ ተወዳዳሪዎች በመሆናቸው ነው።
ዝርዝር ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር
ልደት አበበ