1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

2016 በስፖርቱ ዓለም

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2009

በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን አቆጣጠር 2016ዓ,ምን ጨርሰን 2017 ን ለመያዝ የቀሩን በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ናቸው። ይህ የምንሸኘው ዓመት በስፖርቱ ዘርፍ በርካታ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ አስደሳች እና አስግራሚ ክስተቶች የታዩበት ነበር።

https://p.dw.com/p/2Ut5M
Äthiopien Leichtathletik-Legende und zweifacher Olympiasieger Miruts Yifter ist gestorben
ምስል Hanna Demise

2016 በስፖርቱ ዓለም

ኢትዮጵያን በቅድሚያ ስንመለከት ከአስደሳቾቹ መካክል የአትሌት አልማዝ አያና ምትሀታዊ ፍጥነት እና አጨራረስ ፣ የአትሌቲክስ ፊዴሬሽን ለመጀመርያ ጊዜ የኃላፊነት ስልጣኑን  ለዘርፉ ባለሙያዎች ዕድል ለመስጠት መወሰኑ ሲጠቀሱ ። የዚካ ቫይረስ የሀገሪቱ የውስጥ ፖለቲካ እና ፀጥታ እንዲሁም  የአበረታች ንጥረ ነገር መጠቀም ሲያወዛግበዉ በከረመው በ31ኛው የሪዮ ኦሎምፒክ  የሮቢል ኪሮስ ውኃ ዋና ስፖርት ውድድር አና ውጢቱ አስግራሚ አና አነጋጋሪው ነበር። በአሳዛኝነታቸው ከሚወሱት መካካል  የአትሌት ሻንበል ምሩፅ ይፍጠር  የዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ አንዲሁም የ ሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት በሞት መለየት ይጠቀሳሉ።   በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ  በ እንግሊዝ ፕርምየር ሊግ አስደናቂው የ ሊስትር ሲቲ የፕርምየር ሌግ ሻንፒየን መሆን፣ በደጋፊዋች ሁከት ሲናጥ  የነበረው  በፈረንሳይ የተስተናገደው የ2016 የአውሮጳ ዋንጫ፣ አስተናግጅዋን ሀገር  ድል ነስቶ የፖርቹጋል ብሂራዊ ቡድን አሸናፊ መሆን፣ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በአይስላንድ በኣሳፋሪ ሁኔታ ተሽንፎ ከውድድሩ መውጣት ፥  እንዲሁም  የሙስና ቅሌት  በ እግርኩዋስ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካክል እና ለብራዚል ተጫዋቾቹን ህይወት ህልፍት ምክንያት የሆነው  አሳዛኝ  የአውሮፕላን አደጋ ጎልተው ይጠቀሳሉ።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ