James Muhandoቅዳሜ፣ ጥር 3 2017የሌሎቹ ብልሆች ድራማ አራተኛ ክፍል አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ (AI) እንዴት ዓለማችንን እየቀየረ እንደሆነ ይመለከታል። ባለፈው ክፍል የኢንዙና መንግሥት ከAI ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ አግዷል። በወቅቱ አይናቸውን በምስጢራዊ ዲጂታል ማሽን ስካን ሲደረጉ ገንዘብ የሚከፍለው ግሎባል ትሬዠር የተባለ ኩባንያ በግል መረጃ ስርቆት እገዳ ተጥሎበታል። ይኸ በእንዲህ እንዳለ የራሒም ዲጂታል ረዳት ካቪንዱ ኢንዙና በተፈጥሮ ቁጣ ልትመታ ነው የሚል ትንበያ እየሰጠ ነው። የካቪንዱ ትንበያ ምን ያክል ትክክል ነው? ወይስ እምነት እንደምትለው የጥፋት ነብይ ነው? “የሆነ ነገር ልክ አይደለም” የተሰኘው አራተኛ ክፍል ምላሽ አለው።