1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሲዳማ 11.11.2011 እና ጠ/ሚ ዐቢይ በኤርትራ

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011

በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ አቀንቃኞች የተሰጠው እና ፤ በስጋት ከተጠበቀው የሐምሌ 11 2011 ቀጠሮ ደርሶ ግጭት ጉዳት እየተሰማበት ነው። የጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ ለጉብኝት ኤርትራ ዘልቀዋል፤ ጉብኝታቸው የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎችንም አነጋግሯል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ  የክብር ዶክትሬት መስጠቱም አወያይቷል።

https://p.dw.com/p/3MLiT
Äthiopien Ethnie der Sidama
ምስል DW/S. Wegayehu

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

 

በደቡብ ኢትዮጵያ የተነሳው የክልልነት ጥያቄ፤ ላይ የድጋፍ አስተያየቶች የመሰጠታቸውን ያህል ከሀገር ህልውና አኳያ ሰከን እንዲባል የመከሩም ጥቂት አይደሉም። በፌስቡክ ቶልቻ ጀቤሳ ጉርሜሳ፤ «መብታቸው ነው ። ሕገ መንግሥቱ የሚፈቅደውን መብት ሕጋዊ ነው። ሊከበርላቸው ይገባል።» ሲሉ ደሲድ ማኒድ፣ «በጣም ፤ በጣም እጅግ በጣም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡ Viva Sidama, ሲዳማ አቃፊ ህዝብ ነው፡፡ » በማለት ይጀምሩ እና ስድብን አክለው አስተያየታቸውን ቋጩ። ገነነ ዲማም በዚሁ በፌስቡክ፤« ጥያቄው ተገቢ ቢሆንም ነገር ግን ድሞክራሲን ባማከለ ቢሆን ምን ኣለበት? ቆም ብለን ቢናስብበት አይሻልም ? አረ ሰው ለምን ይሙት» በማለት ተማፀኑ።

ጉበና ፈንታው በበኩላቸው፤ «ጎበዝ ሕገ መንግሥቱ ነው ችግሩ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በፈለጉበት ሰአት ክልል የመሆን መብት ኣለቸው ይላል። ስለዚህ  ከ80 ክልል በተጨማሪ ወለጋ፣ ባሌ፣  እንደርታ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣  ሸዋ ፣ ጎንደር ወዘተ ክልል ቢጠይቁ መብታቸው ነው ደግሞም  ጅማሮ  አለ።» በማለት ገላጋይ የመሰላቸውን ሃሳብ ሰነዘሩ።

«ክልል ምንድን ነው በዚህ ዘመን? ኢትዮጵያ ሀገሬ መት 100 ሺ ዜጎች  በዮንቨርስቲ  በሚመሩቁባት ሀገር  ስለማርስ ማሰብ  ሲገባቸው በጎጥ  ይጣላሉ አስተ በመጽሐ  የተ ያንተ ጎጥ ሳይሆን የሁላችን ሀገር ኢትዮጵያ ናት።» ያሉት ደግሞ ደጀኔ ታምሩ ናቸው በፌስቡክ።

ማናኤላ ኢስማኤል የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ «እውነት ነው ክልል የመሆን ጥያቄ መጠየቅ ሕገ መንግሥታዊ መብት ነው ፣ ነገር ግን እንደተባለው በኃይልና በጉልበት ለማሰፈፀም መነሳት ደግሞ ወንጀልም ነው ፣ ሀገርንም የሚጎዳ አካሄድ ስለሆነ ፣ እኔ እንደ አንድ ዜጋ አወግዛለሁ ።» ይላሉ።

Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል DW/S. Wegayehu

ነገሩ የተጣደፈባቸው የሚመስሉት ሸዋለም ችሮታው ደግሞ በፌስ ቡክ፦ «እዚች ሀገር ሁሉ ነገር ሱሪ በአንገት ሆነ በቃ ? ወይ ጉድ» ሲሉ ትዝብታቸውን አጋርተዋል። ካሣ ጄማሞ፤ «ገዢው ፓርቲ ወይም መንግሥት ለዚህ 100 በመቶ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው» ይላሉ። ፈለቀ ነመራ ባዩ በበኩላቸው፤ «የሰው ደም ፈሰሰ አሁን መንግሥት ከክልልነት ጥያቄ በተጨማሪ ሌላ የቤት ሥራ ተሰጠው አጣርቶ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ ተጎጂዎችን መካስ ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ደም ካልፈሰሰ ፖለቲካው ፖለቲካ የማይመስላቸው አረመኔዎች ናቸው።  የሚናገሩትን የማያውቁ ተማርን ባዮች በቴሌቪዥንና በዩቲዩብ መስኮት ብቅ እያሉ መርዛቸውን ይረጩና ምንም የማያቀው ምስኪን ይታረዳል።» ሲሉ ዘለግ ያለ አስተያየት በፌስቡክ አጋርተዋል።

ሌላው የማኅበራዊ መገናኛዎች መነጋገሪያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኤርትራ ጉብኝት ነው። ሊና ደረጀው በፌስቡክ « እሱ በወጣ ቁጥር እዬተጠበቀ የሚደረገው ጥፋት ምንም እውነቱ ግልፅ አልሆነልንም? ሲቀጥል ደግሞ 18 ባንክ ዘርፎና ሀገርን በጥብጦ በሰላም ተከብረው በሚኖሩባት ሀገር ምንም የማያ ምስኪኖች እየለዩ ማሰርስ ምንድነው? ይሄ ነው እኩልነት ? ይሄ ነው ፍትህ?» ሲሉ፤ ቦናንዛ ዘ ኃይሉ የተባሉት ደግሞ በዚሁ በፌስቡክ፤

ታዝ ታዝ ደግሞ «እሱ ከመዉጣቱ በፊት» ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማለት፤ «እሱ ከመውጣቱ በፊት ሀዋሳ ላይ 11/11/11 ምን ሊሰራ እንደታቀደ በቂ በመረጃ ነበረ ። አይደለም አብይ እኔ የማውቀው እራሱ ብዙ ነው ።» አሉ። 

አላሁ አክበር የሚል የፌስቡክ ያላቸው ሌላው አስተያየት ሰጪ ቀደም ላሉት አስተያየቶች ምላሽ በሚመስል፤ «አትጠራጠር  ሳትወዛገብ  ሀቅን  ተቀበል  ዐቢ ፈጣሪ መሰለህ    አገር እሚጠብቀዉ?  እርሱ  የሚለውን  ሁሉም  በረሰብ  ቢተገብር  አንድም  ባልሞተ ነበር ። ሥልጣን  አገኛለሁ  እያለ  እሚስገበገበው  ሁሉ  በሞተ ቁጥር  ዐቢይ ዐቢይ አትበል።» ብለዋል።

Eritrea Architektur in Asmara
ምስል Reuters/T. Mukoya

አብርሃ በላይም ፤ «ዶ/ር ዐቢይ ዛሬም ተመልሰው ወደ ኤርትራ ሄደዋል። የሄዱት ስለ ችግር ለማውራት እንጂ ለሽርሽር እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ግን እውነት ኢሳያስ ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሄ ይሆናሉ? ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መፍትሄው በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ እንጂ በኢሳያስ እጅ ላይ አይደለም። ኢሳያስማ የራሳቸው አገርም በተቃውሞ እየታመሰች ነው። የኤርትራው አምባገነን መሪ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ጭስ ካዩ፣ ቤንዚን ያቀብሉ እንደሆን እንጂ፣ በሌላ አይታሙም። «ወይ መካሪ ማጣት!» እንዳንል የዐቢይ አማካሪዎች ነቃ በሉ!» በማለት አስተያየታቸውን በፌስቡክ አካፈሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የአስመራ ጉብኝት የኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የኤርትራውያንንም አስተያየት ግብዟል። ፎቶዎችን አስደግፈው በትዊተር ከተሰጡ አስተያየቶች፤ ሙሴ ስብሀቱ እንዲህ ይላሉ፤ «የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ካለፍርሃት ሰላም በሰፈነባት አስመራ ከተማ ሲራመዱ። ዐቢይ አህመድ ከራሱ ከተማ ከአዲስ አበባ ይልቅ አስመራ ውስጥ ደህንነት እንደሚሰማው እወራረዳለሁ።»

ሰላም ኪዳኔም በትዊተር፤ «እነዚህን ሁለት የድራማ ንግሥቶች ሰላምን በተግባር የማስፈን ጊዜው አሁን መሆኑን እባካችሁ ንገሯቸው። ድራማው ይብቃ! ሕጉን ተግባራዊ አድርጉ እና ሳዋ ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መሰጠቱ ይብቃ።» በማለት ጠይቀዋል።

ሚለና በረከት ደግሞ፤ «ይህ የጥንዶቹ ልብ የሚያሞቅ ትስስር ግልፅ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው። የአገሮቻችንን የልማት ጎዳና፤ እድገታችንን፣ የወደፊት ትውልዶችን ዕጣፈንታ ፣ ደህንነት ወዘተ,,, ሁሉም ደግሞ ዛሬ በሚደረገው መተማመን እና ቀጥ ባለው ጉዞ ነው።» ብለዋል።

Äthiopien Addis Abeba Muslime Feiern Eid Al-Fitr
ምስል DW/G. Tedla

አልማዝ ዘራይ በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የልዑካን ቡድናቸው አስመራ ጎዳና ላይ ሲጓዙ የሚያሳይ ፎቶን አስደግፈው፤ «ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ካርሸሊ ወህኒ ቤትን እንዲጎበኙ ንገሯቸው ከአልባ ቢስትሮ በእግር 15 ደቂቃ ብቻ ነው የሚያስኬደው።»ካሉ በኋላ «የአክል ኤርትራ! ኤርትራ ይብቃ!» የሚል መልእክታቸውን ሲያጋሩ፤ ለእሳቸው መልክት ምላሽ፣ ስዩም ፀሐዬ እንዲህ ሲሉ ሰጡ፤ «ደካማ ፕሮፓጋንዳ! ትክክለኛ ኤርትራውያን፤ የአስመራ ልጆች ባድመ፣ ፆረና፣ ቡሬ፣ ዛላምበሳ፣ ተሰነይ፣ አዲ በጊኦ፣ ከንሸላዮ፣ ቶኮምቢያ፣ ገዛ ገረሥላሴ፣ ወዘተ እነዚያን ወራሪዎች ሲዋጉ ተቀበሩ። ዐቢይ ያኔ እኛን ሊዋጋ እዚያ ነበር።»

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የክብር ዶክትሬት ለሁለት ዜጎች ሰጥቷል። ማኅበረሰባዊ ክብር ካገኙት በተለይ የአንደኛው እውቅና ማግኘት አብዛኛውን የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚ አዎንታዊ አስተያየት ሲያቀባብል ከርሟል። በዘመኑ የተከሰቱ ኢትዮጵያዊ አዛውንት መገለጫ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ። እሳቸው ለዚህ ሲበቁ ባደረጉት ንግግር በኅብረተሰቡ መካከል ሰላምን ለማስፈን በግል ላደረጉት ጥረት እውቅና አይደለም በጎ ምላሽ አጥተው መቆየታቸውን በማስታወስ ለዚህ የመረጧቸውን አመስግነዋል። ኤብሮ ኮፊ ካታገ በሚል የፌስቡክ ስም የሚጠቀሙ «እርሶ እኮ ልዩ ነዎት» ሲሏቸው  ጴጥሮስ አሸናፊ፤ «ይደልዎ!» ብለዋል በግዕዙ፤ «ይገባቸዋል» እንደማለት። ትዕግሥት ታዬም በፌስቡክ፤ «እውነት ነው እርሶ ጥሩ መካሪ አባት ነዎት ይገባዎታል።» ብለዋል። የለውጡን ማዕበል  ደጋፊ ነኝ የሚል የፌስቡክ ስም ያላቸው ደግሞ፤ እንዲህ አሉ፤

«እኔ  ክርስቲያን  ነኝ  ሆኖም  ግን እኝህን  የተከበሩ  ታላቅ የሃይማኖት  መሪ ፣ እኝህ  የተከበሩ የፍቅርና  የሰላም  ሰባኪ ፤  ሁሌም  እወዳቸዋለሁ።  ከአንደበታቸው  ማር  ነው የሚፈልቅ።  እውነት አላችኋለው  ቀኑን  ሙሉ  ንግግራቸውን  አድምጬ  የማልጠግብ ፤ ለኢትዮጵያ  ሕዝብ  ፈጣሪ  የሰጠን ታላቅ  ሰው ፤ ዘር ሃይማኖት  የማይገድባቸው  የኢትዮጵያ አባት።» በማለት ረዥም ዕድሜ ተመኝተውላቸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ