1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳምንታዊዉ ስፖርት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2007

ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ 2014 ዓ,ም የሚካሄዱት አብዛኞቹ የስፖርት ዉድድሮች የአሮጌዉን ዓመት ዉድድራቸዉን አካሂደዉ ግማሹ በደስታ ገሚሱ ደግሞ በሀዘን ለገናና ለአዲሱ ዓመት የአንድ ወር እረፍት ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/1E8kE
Bundesliga Hertha BSC - 1899 Hoffenheim 21.12.2014
ምስል picture-alliance/dpa/Gambarini

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ ተጋርቶ መዉጣቱ ደጋፊዎቹን አስቆጭቷል። አሰልጣኝ ፔሌ ግሩኒ የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ህልም ቅዠት እንዳልሆነ አስመስከረዋል። ዌስትሃሞች በታሪካቸዉ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ አራት ዉስጥ ተቀምጠዉ ዓመቱን ሸኝተዋል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ደግሞ ሆፍናም ሃርተን በሜዳዉ አምስት ለዜሮ ቀልዶበታል። ብሬመን ዶርትሙንድን ቢያሸንፍም ሁለቱም ዉድድሩ ሲጀመር ባላሰቡት የቡንደስሊጋዉ የወራጅ ቀጣና ተቀምጠዉ የዓመቱን ዉድድራቸዉን ጨርሰዋል። ፊፋ ሲወቀስበት የከረመዉን የሙስና ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ማይክል ጋርሲያን የምርመራ ዘገባ ይፋ እንዲሆን ወስኗል። የአፍሪቃ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመጪዉ ዓመት የሚካሄደዉን ከሃያ ዓመት ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የሚደረገዉን የወጣቶች እና የታዳጊዎች ዉድድር ድልድል ይፋ አድርጓል። እነኝህና ሌሎች የስፖርት ዘገባዎችን ያካተተዉን ጥንቅር ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ።


ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ