1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስቶክሆልም-የኤርትራዉያን ግጭት በስዊድን

ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2015

የስቶክሆልሙ ድግስ በሚደረግበት አካባቢ ድግሱን የሚቃወሙ ከአንድ ሺሕ የሚበልጡ ኤርትራዉያን ተሰልፈዉ ነበር። በግጭቱ ከቆሰሉት ቢያንስ 8ቱ ክፉኛ መጎዳታቸዉን የጀርመኑ ዜና አገልግሎት DPA ዘግቧል። ግጭቱን ቀስቅሰዋል የተባሉ 140 ሰዎች ታስረዋል።

https://p.dw.com/p/4UnWJ
Schweden Ausschreitungen bei eritreischem Festival in Stockholm
ምስል Magnus Lejhall/AP Photo/picture alliance

ስዊድን ርዕሠ-ከተማ ስቶክሆልም ውስጥ ትናንት በተዘጋጀ የኤርትራዉያን የባሕል ድግስ (ፌስቲቫል) ላይ በተቀሰቀሰ ግጭትና ረብሻ 52  ሰዎች ቆሰሉ፤ ግምቱ በዉል ያልታወቀ መኪናና ሌላ ንብረት ተቃጠለ ወይም ተሰባበረ። የስዊድን መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት በድግሱ ላይ የታደሙና ድግሱን የሚቃወሙ ኤርትራዉያን ጎራ ለይተዉ በዱላ፣ በተቀጣጣይና ተወርዋሪ ቁሶች ጭምር ሲደባደቡ ነበር። ተደባዳቢዎቹ መኪናና ሌሎች ንብረቶችን በእሳት አጋይተዋልም። በግጭቱ ከቆሰሉት ሦስቱ ፖሊሶች ናቸው። የስቶክሆልሙ ድግስ በሚደረግበት አካባቢ ድግሱን የሚቃወሙ ከአንድ ሺሕ የሚበልጡ ኤርትራዉያን ተሰልፈዉ ነበር። በግጭቱ ከቆሰሉት ቢያንስ 8ቱ ክፉኛ መጎዳታቸዉን የጀርመኑ ዜና አገልግሎት DPA ዘግቧል። ግጭቱን ቀስቅሰዋል የተባሉ 140 ሰዎች ታስረዋል። አዉሮጳ ዉስጥ በተለያዩ ከተሞች በየዓመቱ የሚዘጋጀዉ «የባሕል» የተባለዉ ድግስ «ጨቋኝ» የሚባለዉ የኤርትራ መንግስት ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያደርግበት፣ የመንግሥት ደጋፊዎችና ባለሥልጣናት የሚካፈሉበት፣ ለመንግሥት ገንዘብ የሚዋጣበት ነዉ ተብሎ በተደጋጋሚ ይወቀሳል፤ ተቃዉሞም ይገጥመዋል። ከሦስት ሳምንት በፊት ጊሰን-ጀርመን ዉስጥ በተደረገ ድግስ ላይ በተነሳ ተመሳሳይ ግጭት 26 ፖሊሶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል።
ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ