ስፖርት ህዳር 13፣2008
ሰኞ፣ ኅዳር 13 2008ስኮትላንዳዊው የኬንያ አሰልጣኝ ቦቤ ዊልያምሰን ከዚህ ቀደም ከዩጋንዳ ቡድን ጋር በመሆን የሴካፋን ዋንጫ ወስደዋል።
ምድብ ለ ን ኬንያ ስትመራው ቅዳሚ ዕለት ዛንዚባርን አንድ ለዜሮ የረታው ቡሩንዲ ሁለተኛ ዛንዚባር ሶስትኛ ዩጋንዳ የምድቡ መጨረሻ ነው ።
ከምድብ ሀ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ታንዛንያ ሱማልያን 4 ለ 0 ረተወል ። በመሆኑም ምድብ ሀ ን ታንዛንያ ስትመራው ቅዳሜ በመክፈቻው ጨዋታ ኢትዮጵያን አንድ ለዜሮ የረታው ርዋንዳ ሁለተኛ፡ አስተናጋጅዋ ኢትዮጵያ ሶስተኛ ሶማልያ አራተኛ ናቸው።
ቀጣይ የሴካፋ ውድድር በባህርዳር ስታድየም ደቡብ ሱዳን ከጅቡቲ ሱዳን ከማላዊ ዛሬ በሚያድርጉት ጨዋታ ቀጥሎ ይውላል።
ምድብ ሀ |
||||||||
ደረጃ |
ቡድን |
ተጫ |
አሸ |
አቻ |
ተሸ |
አገ |
ገባ |
ነጥ |
1 |
ታንዛንያ |
1 |
1 |
0 |
0 |
4 |
0 |
3 |
2 |
ሩዋንዳ |
1 |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
3 |
3 |
ኢትዮጵያ |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
1 |
0 |
4 |
ሱማሌያ |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
4 |
0 |
ምድብ ለ |
||||||||
ደረጃ |
ቡድን |
ተጫ |
አሸ |
አቻ |
ተሸ |
አገ |
ገባ |
ነጥ |
1 |
ኬንያ |
1 |
1 |
0 |
0 |
2 |
0 |
3 |
2 |
ቡሩንዲ |
1 |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
3 |
3 |
ዛንዚባር |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
0 |
0 |
4 |
ዩጋንዳ |
1 |
0 |
0 |
1 |
0 |
0 |
0 |
ምድብ ሐ |
||||||||
ደረጃ |
ቡድን |
ተጫ |
አሸ |
አቻ |
ተሸ |
አገ |
ገባ |
ነጥ |
ሱዳን |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
|
ማላዊ |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
|
ደቡብ ሱዳን |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
|
ጅቡቲ |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
0 |
ጉልበት ሰጭ እፅ ወስደዋል የተባሉ ሁለት የሩስያ አትሌቶች ከአበረታች እፅ ንፁሕ ነን፣ ይህንንም ለማረጋገጥ ወደ ሕግ እንሄዳለን ሲሉ ተናገሩ ።
የ1500 ሜትር ሯጭ ክሪስቲና ኡግሮቫ እና የ800 ሜትር ሩዋጭ ታቴያና ማያዚና አትሌቲከ ውድድር እንዲታገዱ ባለፈው ሳምንት በአለም አቀፉ አትሌቲከ ማህበርየ ፀረ አበረታች እፅ ተቋ ም ሀሳብ ከቀረበባቸው አምስት የሩስያ አትሌቶች መካከል ናቸው።
በጀርመን ቢንዲስሊጋ አስራ ሶስትኛው የጨዋታ ቀን፣ በስፔን ላሊጋ አስራ ሁለተኛው የጨዋታ ቀን፣ በእንግሊዝ ባርክሌየ ፕርሚየርሊግ አስራ ሶስትተኛ ቀን ጨዋታ፣ በኢጣልያ ሴሪያ ኤ፣ ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽የደረሰውንየእሸባሪያችጥቃርረብባያገናኝ በፈረንሳይ ሊግ ዋን እና በሌሎችም የአውሮፓ ሀገራት በሳምንቱ መጨረሻ የተደረጉ ጨዋታዎች የተጀመሩት ባለፈው ሳምንት አርብ በፈረንሳይ በደረሰው የእሸባሪያች ጥቃት ህይወታቸውን ላጡት አንድ መቶ ሰላሳ ሰዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ በተደረገ በአንድ ደቂቃ የኅሊና ፀሎት ነው ።
የሚዳ ቴኒስ
ኖቫክ ጆኮቪች ሮጀር ፌደረርን በማሸነፍ የአለም ዙር የሜዳ ቴንስ ውድድር አሽናፊ ሆነ ።
በሜዳ ቴኒስ የአለም ቀዳሚ ሰርቢያዊው በለንደን ኦቱ አሬና ትላንት በተደረገ ውድድር ተጋጣሚውን በሰማንያ ደቂቃ ውስጥ 6ለ 3 እና 6ለ 4 ነው የረታው የ ሀያ ስምንት አመቱ ጃኮቬች በዘንድሮ አመት ሶስት የ«ግራንድ ስላም»ን ጨምሮ አስራ አንድ ውድድሮችን በድል አጠናቅዋል።
ሀና ደምሴ
አርያም ተክሌ